በሀገራዊ የኤች.አይ.ቪ ግምትና ትንበያ (Estimation and projection) ሂደት ላይ ለክልል ጤና ቢሮ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ወርክሾፕ ተካሄደ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተላላፊ በሽታዎች ምርምር (የኤች. አይ. ቪ እና ሌሎች የአባላዘር በሽታዎች ክፍል) ከጤና ሚኒስቴር፣ UNAIDS እና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የ2026 የኤች.አይ. ቪ ግመታ አሠራር ላይ ከክልሎች ለመጡ ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረዉ ወርክሾፕ የጤና ሚኒስቴር አቶ ፍቃዱ ያደታ የHIV/AIDS Prevention and Control lead executive officer በተገኙበት ተጠናቀቀ::
ዎርክሾፑ የክልል ጤና ቢሮ ባለሙያዎች በሀገራዊ የኤች.አይ.ቪ ግምትና ትንበያ ሂደት ውስጥ ያላቸውን አስተዋፅኦ ለማጠናከር የተዘጋጀ ነው። ኢንስቲትዩቱ የሀገሪቱን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት ግምታዊ ስሌትና ፕሮጀክሽን ተአማኒነት ይበልጥ ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ታምኖበታል።
በወርክሾፑ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ የተላላፊ በሽታዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ገመቹ ታደሰ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤች.አይ.ቪ ፕሮግራሞች የሚያገኙት የፋይናንስ ድጋፍ እየቀነሰ በመምጣቱ እንደ ሀገር የራስን አቅም ማጠናከርና ትክክለኛ የግምት ስሌቶችን ማዘጋጀት ለሀገራዊ ፕሮግራሙ ስኬት እጅግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
ዶ/ር ገመቹ አክለውም ከክልሎች የሚሰበሰቡ የኤች.አይ.ቪ ፕሮግራም መረጃዎች ለብሔራዊ የግምታዊ ስሌት ስራዎች መሰረታዊ መሆናቸውን ጠቁመው፣ የመረጃ ጥራት መጠበቅ በSpectrum ሶፍትዌር የሚሰሩ የHIV Estimation and Projection ውጤቶች ትክክለኛነት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸዋል።
በኢንስቲትዩቱ ስልጠና ማዕከል የተካሄደው እና ለአምስት ቀናት የቆየው ይህ መድረክ በዋናነት የብሔራዊ የHIV ግምታዊ ስሌትና ፕሮጀክሽን ሂደቶችን ለማሻሻል የሚያስችሉ የግንዛቤ ማሳደጊያ፣ የክህሎት ማበልጸጊያ እና የመረጃ ማረጋገጫ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ተካሂዷል።
በዚህ የምክክር መድረክ የተሳተፉ ባለሙያዎች ስለ HIV ግምታዊ ስሌት ሂደቶች ጥልቅ ግንዛቤ እንዲያገኙ ከመድረጉም ባለፈ እንደ Spectrum/AIM (National and Regional HIV Estimates)፣ Shiny90 (Knowledge of HIV Status Estimation) እና Naomi (Sub-national HIV Indicators Estimation) ያሉ ዘመናዊ የመረጃ መተንተኛ ሞዴሎችና መሣሪያዎች አጠቃቀም ላይ ዝርዝር ውይይት አድርገዋል።
በተጨማሪም ከክልሎች የሚሰበሰቡ የፕሮግራም መረጃዎች እንደ PMTCT፣ ANC HIV Testing፣ ART፣ HIV Testing Services፣ Knowledge of HIV Status፣ Viral Load Suppression እና Key Populations ያሉ ዋና ዋና አመላካቾች ላይ ያሉ የመረጃ ጥራት ጉዳዮችን በመፈተሽ ችግሮችን በዝርዝር ለመለየት ስራ ተሰርቷል።
በወርክሾፑ ሂደት ውስጥ የክልል ባለሙያዎች የቀረቡ መረጃዎችን ከብሔራዊ መረጃዎች ጋር በማነፃፀር የማረጋገጥ ስራ እንዲያከናውኑ ተደርጓል። ይህም የሀገሪቱን የHIV መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራም በተጨባጭ እና በታመነ መረጃ ላይ እንዲመሠረት ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።
በመድረኩ ማጠቃለያም አቶ ፈቃዱ ያደታ በቀጣይ የመረጃ ጥራት ማሻሻያ ዕቅዶች፣ በቴክኒክ መሣሪያዎች አጠቃቀም እና በባለድርሻ አካላት የጋራ ስራ ላይ የሚደረጉ ቀጣይ እርምጃዎች ላይ የጋራ ግብ እንዲኖር አቅጣጫ አስቀምጠዋል። ይህም ኢትዮጵያ የHIV ስርጭትን ለመቆጣጠር የምታደርገውን ጥረት በሳይንሳዊ መረጃና ትንተና የተደገፈ እንዲሆን ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
በመጨረሻም ስለ መረጃ ግብዓቶች እንነዲሁም የመረጃ ጥራት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ከተወያዩ በኋላ ዉይይቱ ላይ ከክልሎች ከዚህ በፊት ሲነሱ በነበሩ ጉዳዮች ላይ ማብራርያ ከተሰጠ በኋላ የወደፊት አቅጣጫ በማስቀመጥ አቶ ፈቃዱ ያደታ ስብሰባዉን ዘግቶዋል።