በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ ለሕብረተሰብ ጤና

በማስረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ ለሕብረተሰብ ጤና ወሳኝ መሆ ኑ ተገልጿል::
በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ (Evidence-Informed Decision-Making – EIDM) ጉባኤ በአድዋ ሙዚየም አዳራሽ እየተካሄደ ሲሆን የጤና ስርዓቶችን በዕውቀት፣ በማስረጃና በትብብር ማጠናከር የወቅቱ ቁልፍ አጀንዳ መሆኑ ተገለጸ።

በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ፣ ጉባኤው የጤና ስርዓቶችን በዕውቀት፣ በማስረጃና በትብብር ለማጠናከር ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቅ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።
ዶክተር መሳይ አክለው እንዳሉት፣ ኢንስቲትዩቱ ከ1924ዓ.ም ጀምሮ በርካታ የሕብረተሰብ ጤና ስራዎችን ሲሰራ እንደነበር አስታውሰው ኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ አገልግሎቶችን በሀገር አቀፍ ደረጃ በማስፋፋት፣ በሥነ-ምግብ ጥናት፣ በሕብረተሰብ ጤና ክትትል፣ በድንገተኛ የጤና አደጋ ዝግጅትና ምላሽ ዘርፎች ጉልህ ሚና በመጫወት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ስርዓት ዋነኛ ምሰሶ ሆኖ መቆየቱንም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም በሀገር ደረጃ አንጋፋ ተቋም በመሆን በአፍሪካ ደረጃም የልህቀት ማእከል መሆኑን ገልጸዋል።
የዘንድሮው ጉባኤ ከኢንስቲትዩቱ ተልዕኮና ስትራቴጂያዊ እቅድ ጋር በቅርበት የተሳሰረ መሆኑን የገለጹት ዶክተር መሳይ፣ ኢንስቲትዩቱ ከተለያዩ ምንጮች የጤናና ከጤና ጋር ተያያዥ መረጃዎችን በመሰብሰብ ብሔራዊ የጤና መረጃ አስተዳደርና ቅመራ ትንተና ማዕከል የማቋቋምና የማስተዳደር ኃላፊነት እንደተሰጠው አስታውሰዋል።
በተጨማሪም ብሔራዊ የጤና መረጃ አስተዳደርና ቅመራ ትንተና ማዕከሉ የጤና መረጃዎችን በመሰብሰብ ብቻ ሳይሆን በማደራጀት፣ በደህንነት በመጠበቅ በማስተዳደርና ወደ ተግባራዊ ማስረጃ በመቀየር ለውሳኔ አሰጣጥ እንደሚያገለግል ገልጸዋል። በተለይም የሰው፣ የእንስሳትና የአካባቢ ጤናን በሚያስተሳስረው የ”አንድ ጤና” አቀራረብ ውስጥ የዲጂታል ማከማቻዎች የተለያዩ ማስረጃዎች የሚገናኙባቸው ወሳኝ ስፍራዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የብሔራዊ የጤና መረጃ አስተዳደርና ትንተና ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር ትግስት ሹመት በበኩላቸው፣ አውደ ጥናቱ መረጃን ለጤና ፖሊሲ ግብዓት፣ማስረጃ ተኮር ውሳኔ አሰጣጥ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ዶክተር ትግስት ማብራሪያ፣ ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ወቅት ከ600 በላይ የሚሆኑ የጤና እና ጤና ነክ መረጃዎችን በመሰብሰብ፣ በማደራጀትና በማከማቸት ለሀገራዊ የጤና ውሳኔዎች ግብዓት እያደረገ ይገኛል። እነዚህ መረጃዎች በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር፣ የጤና ፖሊሲዎችን ለመቅረጽ እና በማስረጃ ላይ የተመሰረቱ ውሳኔዎችን ለማሳለጥ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው።
ዶክተር ትግስት አክለውም፣ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጀምሮ የተደራጁ የጤና መረጃዎች የተለያዩ የጤና ስጋቶችን እና ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር በተደረጉ ትንተናዎች እና ምላሾች ውስጥ በቀጥታ አስተዋጽኦ እንዳበረከቱ ገልጸዋል።
የመረጃ ልውውጥና ትብብርን ለማጠናከር ከ195 በላይ የመንግሥት፣ የግል፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች በመረጃ አሰባሰብ ላይ እንዳሉና መረጃ ልውውጥ ዙሪያ የተቀናጀ ትብብር ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
ተናጋሪዎቹ በጋራ ያስተላለፉት መልዕክት፣ የተጣራና የተደራጀ መረጃን ወደ ተግባራዊ ማስረጃ በመቀየር በጤና ዘርፍ የሚሰጡ ውሳኔዎች በታማኝ መረጃ ላይ እንዲመሰረቱ ማድረግ የጤና ሥርዓቱን ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑን ነው።
በጉባኤው ከጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI)፣ ከአርማወር ሀንሰን የምርምር ተቋም (AHRI)፣ ከጤና ሚኒስቴር ስር ካሉ ኤጀንሲዎች፣ ከፌዴራል ሆስፒታሎች፣ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከአጋር ተቋማት የተውጣጡ ተመራማሪዎች፣ ፖሊሲ አውጭዎች፣ የፕሮግራም መሪዎችና ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
The 2026 Evidence-Informed Decision-Making (EIDM) Conference officially opened in Addis Ababa at the Adwa Victory Memorial Museum Hall, bringing together health leaders, policymakers, researchers, and stakeholders to strengthen the use of evidence in Ethiopia’s health system. The conference aims to promote data-driven decision-making and foster collaboration among institutions working to improve public health outcomes across the country.
Opening the event, Ethiopian Public Health Institute (EPHI) Director General Dr. Mesay Hailu said the conference reflects a shared commitment to advancing health systems through knowledge, innovation, evidence, and partnership. He noted that EPHI has grown into a nationally respected institution and a continental center of excellence, making significant contributions in vaccine production, laboratory services, nutrition research, public health surveillance, and emergency preparedness. Dr. Mesay added that the conference aligns with EPHI’s mandate to manage the National Health Data Management and Analytics Center, which transforms health data into actionable evidence for policymaking and planning.
National Health Data Management and Analytics Center Director Dr. Tigst Shumet said the conference focuses on leveraging data to support health policy development, knowledge management, and evidence-informed decisions. She highlighted that the Institute currently manages health-related data from more than 600 health datas, helping to guide disease prevention, policy formulation, and national health planning. Dr. Tigst called for stronger collaboration among over 195 public institutions, private organizations, NGOs, and universities, while participants emphasized that converting high-quality data into actionable evidence is essential for building a more responsive and resilient health system in Ethiopia.