በኢንስቲትዩቱና በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚ/ር ጤና ዋና መምሪያ መካከል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር እና የላቦራቶሪ አገልግሎት ስራዎችን በጋራ ለመስራት ሰኔ 5/2017 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ ስልጠና ማዕከል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
የመግባቢያ ሰነዱ ዋና ዓላማ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት የሚከሰቱትን የሕብረተሰብ አደጋዎች ለሕብረተሰቡ ጤና አሳሳቢ የሆኑ ክስተቶችን የመከላከያ ሰራዊቱን የተልዕኮ ልዩ ባሕሪ ግምት ውስጥ ያስገባና እንዲሁም የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተልዕኮን ያማከለ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ለመስራት፣ ለመከላከል ፣ በወቅቱ ለመለየት፣ ምላሽ ለመስጠት እና መልሶ ለማቋቋም የሚቻልበትን የትብብር ስራ ለማጠናከር ነው፡፡
ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በኢንስቲትዩቱ እና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር ጤና ዋና መምሪያ መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ አስመልክቶ እንደገለጹት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተሰጠውን ኃላፊነትና እየሰራ የሚገኘውን ተግባራት ጠቁመው፤ ኢንስቲትዩቱ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር ጤና ዋና መምሪያ ጋር የሕብረተሰቡን ጤና ለማስጠበቅ በትብብር በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን፣ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ከመከሰታቸውም አስቀድሞ እንዲሁም ሲከሰቱ ወቅቱን የጠበቀ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ለመስራት፣ ለመለየት፣ ለመከላከል፣ ምላሽ ለመስጠት እና መልሶ ለማቋቋም ይቻል ዘንድ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር በመተባበር የተሻሉ ስራዎችን በመስራት የሕብረተሰቡን ጤንነት ለማረጋገጥ የተካሄደ የመግባቢያ ሰነድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሌ/ጄነራል ጥጋቡ ይልማ የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኃላፊ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በእድሜ አንጋፋና በጤናው ዘርፍ በሁሉም ቦታ የሕብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅና የጤና አደጋ የሆኑ ችግሮችን ለመከላከል ከፍተኛ ስራ እየሰራ የሚገኝ ተቋም መሆኑን፣ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊትም አገርን ከተለያዩ ችግሮች የመከላከል ስራ እየሰራ ስለሚገኝ እነዚህ ሁለት ተቋማት የሕብረተሰቡን ደህንነት በማስጠበቅ ደረጃ በጋራ በርካታ ስራዎችን ሲያከናውኑ የቆዩ በመሆናቸው በሁለቱ ተቋማት መካከል የተካሄደው የመግባቢያ ሰነድ በቀጣይ በሚሰሩ የጋራ ስራዎች የበለጠ ለማጠናከርና የተሻሉ ውጤቶችን ለማስመዝገብ የሚያግዝ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እና ሌ/ጄነራል ጥጋቡ ይልማ የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኃላፊ ተቋማቱን በመወከል የመግባቢያ ሰነዱን የተፈራረሙ ሲሆን የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የኢንስቲትዩቱን የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ማዕከልን እና የተለያዩ የላቦራቶሪ ክፍሎችን ጎብኝተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር ጤና ዋና መምሪያ መካከል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ
————————
በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሚኒስቴር ጤና ዋና መምሪያ መካከል የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር እና የላቦራቶሪ አገልግሎት ስራዎችን በጋራ ለመስራት ሰኔ 5/2017 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ ስልጠና ማዕከል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡