በኢንስቲትዩቱ የ NovaSeq X Plus ስልጠና ተሰጠ

September 6, 2025
የኢትዮጰያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአሜሪካው ሉሚና ባዮቴክኖሎጂ ካምፓኒ እና ከአጋሩ የኢትዮጵያው ሬቲና ፈርማሲቲካልስ ጋር በመተባበር በጤና ሚኒስቴር የግሎባል ፈንድ ድጋፍ የNovaSeq X Plus አጠቃቀም ከነሐሴ 26 እስከ 30/2017 ዓ.ም የሚቆይ ስልጠና በኢንስቲትዩቱ ለተቀናጀ የጂኖሚክስ እና ባዮኢንፎርማቲክስ ማዕከል በመስጠት ላይ ይገኛል።
ስልጠናው የቲዎሪ እና የተግባር ስልጠናዎችን በመስጠት የኢንቲትዩቱን ተመራማሪዎች እና የቴክኒክ ባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት ያለመ ነው። በተጨማሪም ለጂኖሚክስ፣ የበሽታ ወረርሽኝ ምርመራዎች እና የባዮኢንፎርማቲክስ ምርምሮችን የላቀ ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር የኢንስቲትዩቱን ብቃት ይገነባል።
ዶlር አብርሃም አሊ በኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ተመራማሪ እና የስልጠናው አስተባባሪ እንደገለጹት ይህ ትብብር ኢንስቲትዩቱ ይህንን የምርምር ዘርፍ በኢትዮጵያ በሚፈለገው መጠን ለማሳደግ እና ከክልል አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ለጂኖሚክ እድገት አስተዋፅዖ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።