በጤና ኬላ ለሚሠጠው ፈጣን የወባ ምርመራ (Malaria RDT) ምርመራ ሒደት ጥራት ፍተሻ ማስጀመሪያ መረሐ ግብር ተካሄደ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወባ ወረርሽኝን ለመከላከላና ለመቆጣጠር ለሚደረገው ቅንጅታዊ ስራ ሊያግዝ የሚችል የፈጣን ወባ መመርመሪያ ጥራት ቁጥጥር ናሙና በማዘጋጀት በሀገሪቱ የሚገኙ ጤና ኬላዎችን አሰራር ለመገምገም የሚያስችል የሙከራ መርሀ ግብር ከሚያዝያ 2 እስከ 3/2017 በአዳማ ከተማ ማስጀመሪያ መረሐ ግብር አካሄደ።
በማስጀመሪያው መረሐ ግብር ላይ የተገኙት የላብራቶሪ አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት የላቦራቶሪ ምርመራ ሂደት ፍተሻና ክትትል ዲቪዢን ዴስክ ሃላፊ የሆኑት አቶ ነጋሽ ኑር አህመድ በንግግራቸው እንደገለፁት ይህ ጅምር በመላ ሀገሪቱ በተለይም ወባ የህብረተሰብ ጤና ተግዳሮት ሆኖ በቀጠለባቸው በገጠር እና በቂ አገልግሎት በሌላቸው አካባቢዎች የወባ ምርመራ ትክክለኛነት እና አስተማማኝነት ለማሳደግ ያለመ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም የወባ ወረርሽኝን በመከላከልና በመቆጣጠሩ ረገድ የምርመራ ጥራት ቁጥጥር ማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው የሚታመን መሆኑን ገለጸው በምርመራ ጥራት ቁጥጥር ስራው ላይ ያሉ ሁሉም ባለድረሻ አካላት የበኩላቸውን ጥረት እዲያድረጉ የሚጠበቅ ሲሆን በተለይም የክልል የወባ ፕሮግራም አስተባባሪዎች እና ላብራቶሪዎች ጥራት ቁጥጥር ናሙናዎችን በመውስድ እና ባለሙያዎችን በማብቃት ስራ ላይ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው እና ይህንንም እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል።
በመርሀ ግብሩም ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ የክልል ላቦራቶሪዎች ወባን ከመከላከል አንፃር የሚሰሩ ስራዎችን እና ጥራትን ለማረጋገጥ ሊያግዝ የሚችል አጠቃላይ መመሪያ የጥራት ፍተሻ ኦፊሰር እና የፕሮግራም አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ወንድሜነህ ልቅናዉ እና በአቶ አብዱልፈታ ከድር በኩል ስልጠና ማብራርያ ተሰጥቷል፡፡