የላቦራቶሪ ጥራት አስተዳደር ስርዓት ሜንተርሺፕ ላይ ለጤና ላቦራቶሪ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከEast Central Southern Africa Health Community (ECSA-HC) ጋር በመተባበርና የላቦራቶሪ ጥራት አስተዳደር ስርዓት (Laboratory Quality Management System) ላይ ከተለያዩ ክልል ለተውጣጡ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች ከውጭ ሀገር በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎችን በECSA-HC በኩል በማስመጣት በላቦራቶሪ ሙያዊ ድጋፍ አሰጣጥ (ሜንተርሺፕ) ላይ ከጥቅምት 10-14, 2018 በአዳማ ከተማ ስልጠና ተሰጠ።
በስልጠናው በWorld Bank-Health Emergency Preparedness Response and Resilient Project (WB-HEPRR) ፕሮጀክት ድጋፍ እያገኙ ያሉ የሆስፒታል-ላቦራቶሪዎች፣ ክክልል የሕብረተሰብ ጤና ተቋማት/ላቦራቶሪዎች እና በኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ ጥራት ትግበራ ዲቪዥን ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎች በስልጠናው ተሳትፈዋል።
በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ተገኘተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሮ አብደላ እንደገለጹት ይህ ስልጠና የላቦራቶሪ ጥራት አስተዳደር ስርዓትን የበለጠ ለመተግበርና አለም አቀፍ የጥራት እውቅና ለማግኘት የሚኖረው ሚና ትልቅ መሆኑን በመጥቀስ ሰልጣኞች ስልጠናውን ወደ ተግባር መለወጥና ያገኙትን እውቀትና ክህሎት ለሌሎች ባለሙያዎች ማጋራት እንዳለባቸው ለዚህም አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል ኢንስቲትዩቱ አጠናክሮ እደሚቀጥል የገለጹ ሲሆን አያይዘውም ይህ ሰልጠና በዘርፉ ለማሳካት የተቀመጡ ግቦችን ከማሳካት አንጻር ያለው ፋይዳ ትልቅ በመሆኑ፣ ለስልጠናው መሳካት እና አስፈለጊውን የስልጠና ግብዓቶች ድጋፍ ላደረገው ECSA-HC ትልቅ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በስልጠናው ላይ የተገኙት የECSA-HC ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ባስተላለፉት መልዕክት ECSA-HC በአፍሪካ የላቦራቶሪ ጥራት አገልገሎትን ለማጠናከር ከሁሉም የአፍሪካ አባል ሀገሮች ጋር በቅርበት እየሰራ ያለ ተቋም መሆኑንና በኢትዮጵያ ለላቦራቶሪ ጥራት አስተዳደር ስርዓት ትግበራና፣ በላቦራቶሪ መሳሪያዎች ጥገና፣ Genome sequencing እና በሌሎች የላቦራቶሪው ዘርፍ ስልጠናዎችን እና ሌሎች ድጋፎችን መስጠት ተቋማቸው አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡