የሕብረተሰብ ትዕይንቶች የጤና ሰጋቶች ልየታ ዳሰሳ የአሰልጣኝዎች ስልጠና ተሰጠ

March 21, 2026
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ትዕይንቶች የጤና ሰጋቶች ልየታ ዳሰሳ የአሰልጣኝዎች ስልጠና ተሰጠ።
በሃገራችን የተለያዩ ሃይማኖታዊ ፤ባህላዊና ስፖርታዊ ክንውኖች የሚካሄዱ ሲሆን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በነዚህ ቦታዎች ላይ የሕብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን አየሰራ ይገኛል፡፡
ኢንስቲትዩቱ ስራዎችን በማዘመንና መረጃን መሰረት ያደረገ የአሰራር ስልቶችን በመዘርጋት አይበገሬ የጤና ስርአትን ለመዘርጋት አየሰራ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ በሀገር ውስጥ ለሚካሄዱ የሕብረተሰብ ትዕይንቶች ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የሕብረተሰብ ጤና ስጋቶችን በመለየት ስጋትን ቀድሞ መቀነስ የሚስችል ሰነድ በማዘጋጀት ከሁሉም ክልል ለተውጣቱ ባለሞያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናው በቀጣይ በሃገሪቱ ለሚካሄደው ሃገራዊ የሕብረተሰብ ትዕይንት ስጋት ልየታ ዳሰሳ ላይ ክልሎች አስፈላጊዉን ሞያዊ ድጋፍ አንዲያደርጉ ብሎም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የአቅድ ክንውን ስራዎችን በማገዝ ይህንን የአሰራር ስልት አስከ ወረዳ ድረስ ለመዘርጋት አንዲችሉ ያግዛል ተብላል።