የኢቦላ ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝ ዝግጁነትና ምላሽን ለመፈተሽ የተግባር ልምምድ

የኢቦላ ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝ ዝግጁነትና ምላሽን ለመፈተሽ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከላት የተግባር ልምምድ (functional simulation exercise) አካሄዱ
EPHI Conducts National Functional Simulation Exercise to Boost Ebola Preparedness and Response Capacity
የተግባር ልምምዱ በብሔራዊ እና በ12 ክልሎች በሚገኙ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከላት በአካል እና በበይነ መረብ ቅንጅት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተካሄደ ሲሆን ዋና ዓላማውም በሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ስርዓት ውስጥ ያለውን የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና የቅኝት አቅምን ለመፈተሽ፣ የዝግጁነት ዕቅዶች ተግባራዊ መሆናቸውን ለመለየት፣ ከክልሎች፣ ከአጋር አካላት እና ከሌሎች ዘርፎች ጋር ያለውን ቅንጅታዊ ትብብር ለመገምገም፣ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ከሌሎች ማዕከላት ጋር ያለውን የመገናኛ ስርዓትን በሚገባ ለማየት እንዲሁም ባጋጠሙ ክፍተቶችም ላይ እርማት በማድረግ የተጠናከረ ዝግጁነትን ለማረጋገጥ ነው።

ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በተግባር ልምምዱ መክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) እና በዩጋንዳ አገራት መከሰቱ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ የብሄራዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል በልዩ ትኩረት ተዘጋጅቶ በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን እና በየብስ መግቢያና መውጫ በሮች እንዲሁም በዓለም አቀፍ አየር ማረፊያዎች ጠንካራ የሆነ የቅኝትና የክትትል ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ስርዓቱን ከማዘመን ባሻገር የጤና ደህንነት ስራችንን ጠንካራ ለማድረግ ይቻል ዘንድ የተግባር ልምምድ በማድረግ ዝግጁነትን በሚገባ በማረጋገጥ ለሚከሰቱ ማንኛውም የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ችግሮች ሁሉ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚቻልበትን አቅም ለመገንባት መሆኑን ገልጸዉ ለዚህም በኢንስቲትዩቱ አመራር በኩል ከፍተኛ ቁርጠኝነት መኖሩን ጠቅሰዋል፡፡
ዶ/ር መልካሙ አብቴ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው እየተካሄደ ያለው የተግባር ልምምድ የኢቦላ ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረግው ከፍተኛ የዝግጅት ወቅት መሆኑ ልምምዱ ከሌላው ጊዜ የሚለይ መሆኑን ጠቁመው፣ ከብሔራዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል እስከ ክልል ድረስ የዝግጁነት አቅማችንን የምንፈትሽበት እና ክፍተቶችን ለመለየት ጠቀሜታዉ የጎላ ሲሆን በቀጣይ በሁሉም ክልል ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል ብለዋል፡፡
ወ/ት ኤቢሴ አቦሴ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል አስተባባሪ አጠቃላይ የተግባር ልምምዱን አስመልክቶ እንደ ተናገሩት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋ (PHE) ባለሙያዎች በፌዴራልና በክልል ደረጃ በተደራጁ 7 ቴክኒካል እና ዋና ዋና ዓላማዎችን መሰረት በማድረግ በአካል እና በበይነ መረብ በተቀናጀ መልኩ የዝግጁነት አቅምን ለመፈተሽ ለ3 ቀናት የተካሄደ ልምምድ መሆኑን ገልፀዉ የነበረው የተግባር ልምምድም እጅግ ውጤታማ እንደነበር አስረድተዋል፡፡
Ethiopian Public Health Institute (EPHI), Conducts National Functional Simulation Exercise to Boost Ebola Preparedness and Response Capacity
The Ethiopian Public Health Institute (EPHI), through the national Public Health Emergency Operation Center (PHEOC), has successfully conducted a comprehensive functional simulation exercise aimed at testing preparedness and response capabilities for a potential Ebola Virus Disease (EVD) outbreak.
Coordinated at the national level, the exercise brought together an extensive network of stakeholders, partners, and 12 subnational PHEOCs representing various regions and city administrations, all participating actively from their respective operation centers. The primary objective of this coordinated effort was to rigorously evaluate the country’s early warning systems, surveillance capacities within the Public Health Emergency Management (PHEM) structure, and the operational readiness of existing contingency plans and procedures.
Beyond internal readiness, the simulation placed a heavy emphasis on multi-sectoral collaboration and seamless communication during a public health emergency. Key focus areas included assessing coordination with regional health bureaus and partners, testing cross-border communication and surveillance at Points of Entry (PoE), and evaluating inter-PHEOC communication networks essential for rapid decision-making. By analyzing information-sharing systems and reviewing critical response measures across major response pillars, the exercise successfully identified system strengths and operational gaps, ensuring a more resilient, synchronized, and timely defense against potential health threats at both national and subnational levels.