የኢትዮጵያን ፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ፕሮግራም ጉዞ የሚዳስስ ጥናት ሊከናወን ነው

የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ብሎም የህብረተሰብ ጤና ዘርፍ በማገዝና በማጎልበት ውጤታማ ይሆን ዘንድ ትልቅ እገዛ ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ ፊልድ ኢፒዲሞሎጂ አድቫንስድ ፕሮግራም በጤናው ዘርፍ ብሎም በህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ላይ ያመጣውን ለውጥ እና እገዛ በተመለከተ ጥናታዊ ግምገማ የሚያደርግ ወርክሾፕ የማስጀመሪያ ፕሮግራም በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ተከናወነ፡፡
በጥናቱ መርሀ ግብር ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ክቡር ዶ/ር አየለ ተሾመ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የኢትዮጵያ ፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ፕሮግራም አሁን ካለበት የተሻለ ሆኖ መቀጠል እንዲችል ብሎም ከሀገሪቷ የጤናው ዘርፍ መርሀ ግብር ጋር ይበልጥ ተቀናጅቶ እንዲሠራ ለማስቻል እንዲቻል ጥናቱ በተጠናከረ መልክ መከናወን እንዳለበት በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡ ክቡር ሚኒስቴር ዴታው አያይዘውም ፕሮግራሙ ቀጣይነት እና የተሻለ ሆኖ እንዲቀጥል ሁሉንም ዘርፎችና ሁነቶች በቃኘ መልኩ እንዲሁም ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የፕሮግራሙ ጉዞ እና ቱሩፋቶች በዝርዝር መጠናት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ዶ/ር መልካሙ አብቴ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ፕሮግራም መኖሩ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከልከል በሚከናወኑ ሥራዎች ውስጥ ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረጉን አውስተዋል፡፡ እንደ ም/ዳይሬክተሩ ገለጻ የፕሮግራሙ መኖሩ ድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ የድንገተኛ ጤና አደጋዎችን ቀድሞ ለማወቅ የሚቻልበትን መንገድ ስልት በ95 በመቶ እንዳሳደገው አስገንዝበዋል፡፡ ም/ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም በቅርቡ በአለምም ሆነ በሀገራችን ተከስቶ የነበረው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተሞክሮ ያስተማረን ነገር ቢኖር በተገቢ ሁኔታ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅቶችን ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ዶ/ር መልካሙ አያይዘውም አሁን ከሚሰራው ጥናት በዘርፉ