የኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል የ6 ወር አፈጻጸሙን ገመገመ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ 6 ወር አፈጻጸሙን ለመገምገም ከጥር 22-23/2017 ዓ.ም. መድረክ አካሄደ።
በመድረኩም የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ፣ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል የሰራ ክፍሎች ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ የተለያዩ ክፍሎች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ መድረኩን ሲያስጀምሩ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት ይህ የግምገማ መድረክ በያዝነው በጀት ዓመት የ6ወር አፈፃፀማችን ምን እንደሚመስል እና የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል በቀጣይ በሚቀሩን ጊዜያት ልንሰራቸው የሚገቡ ተግባራት ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት የሚካሄድበት መድረክ መሆኑን ጠቅሰው፤ በምንሰራቸው ተግባራት ከፍተኛ ስኬት ለማስመዝገብ ሁሉም አካላት የተሰጠውን ተግባር በተገቢው መንገድ ሊተገብር እንደሚገባ ገልጸዋል።
በግምገማ መድረኩም የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል ባሉ የስራ ክፍሎች በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ስድስት ወራት የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት ከተደረገ በኋላ የቀጣይም የስራ ሃላፊነት በአግባቡ በመወጣት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ እንዳለባቸው ተመላክቶ መድረኩ ተጠናቋል።