የኢንስቲትዩቱ የብሔራዊ ቲቢ ረፈረንስ ላቦራቶሪ የልህቀት ማዕከል Center of Excellence ለመሆን የተደረገለት ግምገማ በስኬት ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ የሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት የብሔራዊ ቲቢ ሪፈረንስ ላቦራቶሪ የልህቀት ማዕከልነት ( Center of Excellence /COE/) እውቅና ባለው ሂደት ጠንካራ ግመገም ተካሂዷል።
ጀኔቫ ካለው የአለም ጤና ድርጅት የተወከሉ እንዲሁም ከተለያዩ የአለም አቀፍ ድርጅቶች የተወጣጡ ከፍተኛ ኤክስፐርቶች ያካተተ ቡድን የብሔራዊ ቲቢ ረፈረንስ ላቦራቶሪን፣ የላቦራቶሪውን መሰረተ ልማት፣ የአሰራር ሂደቶች፣ የቴክኒክ አቅም፣ የጥራት አስተዳደር ሰራዓቶችን፣ የሰው ሃይል ብቃቶችን አጠቃላይ ግምገማ አካሂዷል።
ግምገማው በመላው ኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ የላቀ የቲቢ ምርመራ አገልግሎት፣ ስልጠና፣ የምክር አገልግሎት እና ቴክኖሎጂዎችን ለመገምገም በላቀ ሁኔታ የሚሰራና የሚያሰተባብር የቲቢ የልህቀት ማዕከልነት ሆኖ ለማገልገል እውቅና ለማግኝት የተደረገ ነው።
ቡድኑ የላቦራቶሪውን የላቀ የቲቢ መመርመሪያ ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር ላይ ያለውን አፈጻጸም እንዲሁም በውጫዊ ጥራት ቁጥጥር እና አጠቃላይ አፈጻጸም ገምግመዋል።
ዶ/ር ሳሮን አብደላ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር እንደተገለጹት ለልህቀት ማዕከልነት የሚደረገው እንቅስቃሴ የላቦራቶሪ ባለሙያዎችን ትጋትና የአመራሩ ቁርጠኝነት ማሳያ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በራሷም ሆነ በጎረቤት አገራት የቲቢ በሽታን ችግር በጋራና በትብብር ለመቅረፍ ያላትን ዝግጁነት አበክረው ገልጸዋል።
የብሔራዊ ቲቢ ላቦራቶሪ የልህቀት ማዕክልነት እውቅና ከተሳካ የላቀ የቲቢ ምርመራ አገልግሎት፣ እንዲሁም አመራር ለመስጠትና በአጎራባች አገሮች የአቅም ግንባታን ለመደገፍ ያስችላል።
የግምገማው ውጤት በሚቀጥሉት ሳምንታት በአለም ጤና ድርጅት ደረጃ ከተገመገመ በኃላ ውጤቱ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢንስቲትዩቱ የብሔራዊ ቲቢ ረፈረንስ ላቦራቶሪ የልህቀት ማዕከል Center of Excellence ለመሆን የተደረገለት ግምገም በስኬት ተጠናቀቀ
———————-
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የብሔራዊ ቲቢ ሪፈረንስ ላቦራቶሪ የልህቀት ማዕከልነት ( Center of Excellence /COE/) እውቅና ባለው ሂደት ጠንካራ ግምገማ ተካሂዷል።
ጀኔቫ ካለው የአለም ጤና ድርጅት የተወከሉ እንዲሁም ከተለያዩ የአለም አቀፍ ድርጅቶች የተወጣጡ ከፍተኛ ኤክስፐርቶች ያካተተ ቡድን የብሔራዊ ቲቢ ሪፈረንስ ላቦራቶሪን፣ የላቦራቶሪውን መሰረተ ልማት፣ የአሰራር ሂደቶች፣ የቴክኒክ አቅም፣ የጥራት አስተዳደር ስርዓቶችን፣ የሰው ሃይል ብቃትን አጠቃላይ ግምገማ አካሂዷል። ግምገማው በመላው ኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ የላቀ የቲቢ ምርመራ አገልግሎት፣ ስልጠና፣ የምክር አገልግሎት እና ቴክኖሎጂዎችን ለመገምገም በላቀ ሁኔታ የሚሰራና የሚያሰተባብር የቲቢ የልህቀት ማዕከልነት ሆኖ ለማገልገል እውቅና ለማግኝት የተደረገ ነው።
ቡድኑ የላቦራቶሪውን የላቀ የቲቢ መመርመሪያ ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር ላይ ያለውን አፈጻጸም እንዲሁም በውጫዊ ጥራት ቁጥጥር እና አጠቃላይ አፈጻጸም ገምግመዋል።
ዶ/ር ሳሮ አብደላ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር እንደገለጹት ለልህቀት ማዕከልነት የሚደረገው እንቅስቃሴ የላቦራቶሪ ባለሙያዎችን ትጋትና የአመራሩ ቁርጠኝነት ማሳያ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በራሷም ሆነ በጎረቤት አገራት የቲቢ በሽታን ችግር በጋራና በትብብር ለመቅረፍ ያላትን ዝግጁነት አበክረው ገልጸዋል።
የብሔራዊ ቲቢ ላቦራቶሪ የልህቀት ማዕከልነት እውቅና ከተሳካ የላቀ የቲቢ ምርመራ አገልግሎት፣ እንዲሁም አመራር ለመስጠትና በአጎራባች አገሮች የአቅም ግንባታን ለመደገፍ ያስችላል።
የግምገማው ውጤት በሚቀጥሉት ሳምንታት በአለም ጤና ድርጅት ደረጃ ከተገመገመ በኃላ ውጤቱ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
www.ephi.gov.et/news