የኢንስቲትዩቱ የጤና ላቦራቶሪዎች አገልግሎት ዘርፍ የበጀት ዓመቱን የ9 ወር ስራ አፈጻጽም ገመገመ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤና ላቦራቶሪዎች አገልግሎት ሁሉም የዘርፉ ሰራተኞች እና ሌሎች የስራ ክፍል ተወካዮች በተገኙበት የስራ አፈጻጸም የገመገመ ሲሆን፤ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሮ አብደላህ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተሰሩ የጤና ላቦራቶሪ አገልግሎቶችን ከእቅድ አፈጻጸም አንጻር በመገምገም የታዩ ጠንካራ ስራዎችን ማስቀጠል እና ክፍተት የታየባቸውን በፍጥነት ለማረም የሚያስችል እና ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ በተጨማሪም የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያ (Reform) ለባለሙያዎች ከማስገንዘብ አንጻር እየተሰሩ ያሉ በርካታ ስራዎችን በመጥቀስ ይህንንም በይበልጥ መሰራት እንዳለበትም ጭምር አስገንዝበዋል።
በጤና ላቦራቶሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ስር የሚገኙ ሶስቱም ዳይሬክተሮች በየዳይሬክቶሬቱ የተሰሩ ስራዎች ከበጀት ዓመቱ እቅድ አንጻር አፈጻጸማቸውን አስመልክቶ በጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን አብዛኛው ስራዎች ጥሩ አፈፃፀም ማሳየታቸውን አመላክተዋል።
በተመሳሳይ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ተወካይ በጤና ላብራቶሪ አገልግሎት ዘርፍ ስር ያሉ ፕሮጀክቶች አፈፃፀም እንዲሁም የብቃት እና ሰው ሃብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ ስለ የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ማሻሻያ (Reform) አጠቃላይ አሁናዊ ሁኔታ እና ሰራተኛውን የማስገንዘቢያ ገለጻ አቅርበዋል። በመጨረሻም በቀረቡት አፈጻጸሞች እና ክፍተቶች ላይ ተሳታፊዎች ሰፊ ውይይትና ግምገማ በማደረግ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት አስመልክቶ የጋራ መግባባትና አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል፡፡