የውሃ ጥራት ቁጥጥርና ክትትል ላይ ስልጠና ተሰጠ

March 26, 2025
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከመጋቢት 11 እስከ 16/2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ የውሃ ጥራት ቁጥጥር እና ክትትል (Water Quality Monitoring and Surveillance) ስልጠና ስጠ፡፡

ከአማራ ክልል፣ ከጋምቤላ ክልል፣ ከድሬደዋ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኮሌራ በሽታ ተጋላጭ ከሆኑ ስፍራዎች እና የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች አካባቢ የሚሰሩ ባለሙያዎች በስልጠናው ተሳትፈዋል፡፡
በስድስት ቀን ቆይታቸው ተሳታፊዎች የኬሚካል፣ የፊዚካል እና የባዮሎጂካል ውሃ መለኪያ መሳሪያዎች በመጠቀም የውሃ ጥራትን መቆጣጠርና መለካት የሚያስችላቸውን ክህሎት አግኝተዋል።ይህ ስልጠና የሕብረተሰቡን ውሃ አቅርቦት ጥራት ለማሻሻልና አስቀድሞ ውሃ ወለድ በሽታዎች እንዳይከሰቱ ለመከላከል ይረዳል።