EPHI Discussed on It’s First Quarter Performance
The Ethiopian Public Health Institute (EPHI) held a discussion forum on the implementation of the national 3-month plan and the performance of the first quarter of the budget year.
EPHI’s Director General Dr. Mesay Hailu, Deputy Director Generals Dr. Getachew Tollera, Dr. Saro Abdella, Dr. Melkamu Abte along with staffs of the Institute attended the meeting.
Dr. Mesay Hailu, after welcoming the participants exlained that on the meeting there will be discussinons the implementations of the first quarter plan and upcoming activities followed by planning and directions for the next term.
“Due to the occurrence of various natural and man-made disasters in our country; prevention, control and rehabilitation works have been conducted in coordination with the relevant stakeholders. By fulfilling the mission given to us, we should work together to achieve our target,” added Dr. Mesay.
Dr. Getachew presented in detail the document from the Ministry of Plan and Development on the implementation of the national 3-month plan and the results obtained.
Finally discussions on the comments and suggestions were forwarded from the participants and were well addressed.
ኢንስቲትዩቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀሞች ላይ ተወያየ
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሀገራዊ የ3 ወር ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት የሥራ አፈጻጸም ዙሪያ በኢንስቲትዩቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የውይይት መድረክ አካሄደ ።
በዉይይት መድረኩ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና/ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ እንዲሁም ም/ዋና ዳይሬክተሮች ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ፣ ዶ/ር ሳሮ አብድላ እና ዶ/ር መልካሙ አብቴን ጨምሮ ሌሎች የኢንስቲትዩቱ የስራ ሀላፊዎች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል።
መድረኩን የከፈቱት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ በንግግራቸው እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የፌዴራል መንግስት የመጀመሪያ መካከለኛ ዘመን ዋና ዋና ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ፣ በቀጣይ ስለምንሰራቸዉ ስራዎች እና ሊሰሩ ስለሚችሉ ስራዎች ላይ በጋራ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችንና ዕቅዶችን በጋራ በማቀድ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በሀገራችን የተለያዩ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በመከሰታቸው የመከላከል፣ የመቆጣጠርና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሰራቱን ገልፀዋል። አክለውም በአጠቃላይ የተሰጠንን ተልዕኮ በመወጣት በጋራ በመሆን ችግር ፈቺ የሆኑ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በዚሁ መድረክ አይም የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ ሀገራዊ የ3 ወር ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተዘጋጀ ሰነድና በ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ላይ የተሰሩ ስራዎችንና የተገኙ ዋና ዋና ዉጤቶችን በዝርዝር አቅርበዋል ።
በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ ላይ እና በቀሪቡ ሪፖርቶች በመመርኮዝ ከተሳታፊዎች በተነሱ ሃሳቦችና አስተያየቶች ላይ ሰፉ ያለ ዉይይት ተደርጎባቸዋል።