የኢንስቲትዩቱ የNIPN- ኢትዮጵያ አለም አቀፍ ጉባዔ ተካሄደ
በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና አንስቲትዩት የNational Information Platforms for Nutrition (NIPN) ፕሮጀክት 6ኛው ሀገር አቀፍ የስነ-ምግብ መድረክ አለም-አቀፍ ጉባኤ NIPN for the Future: Sustainability in an Evolving Policy Environment’ በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 13-14/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ።
ጉባዔው በይፋ የተጀመረው የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና የኢትዮጵያ የሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉእንዱሁመረ የዘጠኙ የNIPN አባል ሀገራት ኃላፊዎችና ተወካዮች በተገኙበት ነበር።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንደተናገሩት የጉባኤው አጀንዳ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ ነው።
“የኢትዮጵያ መንግስት ከፌዴራል እስከ ቀበሌ ድረስ ያለውን የምግብ እና የስነ-ምግብ አስተዳደር ስርዓትን ዘርግቷል። የምግብና የሥርዓተ-ምግብ አስተዳደሩ የምግብና ሥነ-ምግብ ፖሊሲ አፈፃፀምን የሚያስተባብር ሲሆን፣ የማስፈጸሚያ ስትራቴጂውም በሰቆጣ ዲክላሬሽን እና በምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን መመራት ተችሏል። የNIPN-ኢትዮጵያ ስራ በማስረጃ ላይ የተመሰረተን ውሳኔ በመስጠት የአመጋገብ ፖሊሲዎችን በመቅረጽ ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል፣” በማለት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ወቅደስ አያይዘው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ የሚኒስቴሩ ቴክኒካል ክንፍ እንደመሆኑ የብሔራዊ የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ ስትራቴጂን የመከታተል፣ የመገምገም እና የምርምር ፍላጎቶችን የመከታተል እና የመምራት ኃላፊነት ያለው ነው። በመቀጠልም የኒፕን ስራ በማሕበረሰባችን ጤናና ደህንነት ላይ የሚያመጣው ከፍተኛ ተጽእኖ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
በኢትዮጰያ የጀርመን ኤምባሲ የልማት ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ካርሎታ ፕሪስ በእለቱ እንደተናገሩት፤ መንግሥታቸው በኢትዮጵያ የNIPN ውጥኖችን በማጠናከር በማስረጃ ላይ የተመሰረተ የተመጣጠነ ምግብ ፕሮግራምን በተሻለ መረጃ፣ በፖሊሲ ማስረጃዎችና አቅምን በማሳደግ ዘርፈ ብዙ አቀራረብን ይደግፋል።
ጉባዔው ከዘጠኙ ሀገራት ማለትም ከቡርኪናፋሶ፣ ኮትዲቧር፣ ጓቲማላ፣ ኬንያ፣ ላኦስ፣ ኒጀር፣ ኡጋንዳ፣ ዛምቢያና ከአስተናጋጅዋ ሀገር ከኢትዮጵያ የተውጣጡ ተሳታፊዎችን፣ ለጋሽና ባለድርሻ አካላትን እንዲሁም ሌሎችን ያሳተፈ ነበር።