contact us

Who's Online

We have 257 guests and no members online

merejaየኢንስቲትዩቱ የብሔራዊ የጤና ምርምር መረጃ ማደራጃ ማዕከል ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመረጡ 10 ባለድርሻ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ጋር የጤና ነክ መረጃዎች ወደ ብሔራዊ የጤና ምርምር መረጃ ማደራጃ ማዕከል ተሰብስበው የሚገቡበትንና ጥቅም ላይ የሚውሉበትን መንገድ ለመቀየስ ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡
የውይይቱ ዋና አላማ በሃገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የጤና ነክ መረጃዎች ወደ የብሔራዊ የጤና ምርምር መረጃ ማደራጃ ማዕከል በማምጣት እንዴት ይተንተኑ፣ እንዴትስ ይደራጁና የሃገሪቱ ህግ በሚፈቅደው መልኩ እንዴትስ ይሰራጩ የሚሉትን ሰፊ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ነው፡፡
ዶ/ር ኤባ አባተ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በውይይቱ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ወቅት እንደተናገሩት እጅግ ብዛት ያላቸው ሃገራዊ የጤና መረጃዎች መኖራቸውን፣ እነዚህን መረጃዎች ስራ ላይ የሚያውላቸው የሰው ሃይል መሆኑን ነገር ግን መረጃ በመስጠትና በመቀበል ላይ የሚታጠር ስራ የሚሰራ ከሆነ ዳር ሳይደረስ እንደሚቀርና በጋራ ተናቦ በመስራት ሃገራዊ ፋይዳ ያለው ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባና ለዚህም ኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ቁርጠኝነት እንዳለው በስፋት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ዶ/ር አለምነሽ ሃይለማርያም የብሄራዊ የጤና ምርምር መረጃ ማደራጃ ማዕከል አስተባባሪ ስለ መረጃ መዕከሉ አላማ፣ ስለሚሰራቸው ስራዎችና ስለ አከናወናቸው ተግባራት ከኢንስቲትዩቱ ታሪካዊ አመጣጥ በመነሳት በጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ስለ መረጃዎቹ አሰባሰብ እና አተናተን በቀጣይ ስለሚሰሩት ስራዎች የተግባር እቅድ እንደሚዘጋጅና ስለሚከናወኑት ተግባራት ብሔራዊ የጤና ምርምር መረጃ ማደራጃ ማዕከል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የመግባቢያ ሰነድ እንደሚፈራረሙ ከውይይቱ አስተባባሪዎች መረዳት ተችሏል፡፡
የጤና ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ የሳይት አስተባባሪዎች፣ የኮሌጅ ዲኖች እና የጤና ተመራማሪዎች በአጠቃላይ 32 የተለያዩ ባለሙያዎች በውይይቱ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡mereja2