contact us

Who's Online

We have 285 guests and no members online

godana 1የኢንስቲትዩቱ እንሰሳትና እንሰሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት በአዲስ አበባ በአስሩም ክፍለ ከተማ ለሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች ከህዳር 22 እስከ ታህሳስ 3/2012 የእብድ ውሻ በሽታን አስመልክቶ ሰፊ ስልጠና ሰጠ፡፡
የስልጠናው ዋና አላማ የጎዳና ተዳዳሪዎች በብዛት ከውሻ ጋር ከላቸው ግንኙነት ጋር ተያይዞ በርካታ ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ እየተጠቁ በመሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎች ስለ በሽታው መተላለፊያ እና መከላከያ መንገዱን በስልጠና ግንዛቤ እንዲጨብጡ በማድረግ ከበሽታው እራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ ነው፡፡
በእብድ ውሻ በሽታ መጠቃት ምን ምለት እንደሆነ፣መተላለፊያ እና መከላከያ መንገዶቹን፣በበሽታው የተያዘ ውሻ የሚያሳየው ምልክት ምን እንደሆነ፣ ሰው በዚህ በሽታ ሲያዝ የሚያሳየው ምልክት፣ በበሽታው የተያዘ ሰውን ስንከባከብ የሚደረጉ ጥንቃቄዎች፣ ውሾች አስቀድመው መከተብ እንዳለባቸው ነገር ግን ያልተከተቡ ውሾች ለአደጋው በከፍተኛ ደረጃ የተጋለጡ መሆናቸውን ፣ በበሽታው የተያዘ ውሻን በአፋጣኝ ወደ እንሰሳት ጤና ተቋም መወሰድ እንዳለበት እና ሌሎችም ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ስልጠናው ያተኮረ እንደነበር ስልጠናውን ይሰጡ ከነበሩት የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች ወ/ሮ ፋጡማ ያሲንና ወ/ሮ ትዝታ በቀለ መረዳት ተችሏል፡፡
ስልጠናው በአስሩም ክፍለ ከተማ ለሚገኙ 2127 ለሚሆኑ ጎዳና ተዳዳሪዎች እና 145 ለሚሆኑ ለሰራተኛና ማህበራዊ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን ይህም ከተያዘለት አላማ አንጻር ውጤታማ የሆነ ስልጠና እንደነበር ከስልጠና አስተባባሪዎቹ መረዳት ተችሏል፡፡godana 2JPG