SPAR 2025 እና የNAPHS ወርክሾፕ ተካሄደ

የዓለም አቀፍ የጤና መመሪያ የተቀበሉ አባል አገሮች (States Parties) በየዓመቱ የራሳቸውን የጤና አቅም የሚገመግሙበትና ለዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የሚያቀርቡት አመታዊ ሪፖርት SPAR 2025 እና የብሔራዊ የጤና ደህንነት የድርጊት መርሀግብር (NAPHS) ወርክሾፕ ተካሄደ::
የዓለም አቀፍ የጤና መመሪያ የተቀበሉ አባል አገሮች (States Parties) በየዓመቱ የራሳቸውን የጤና አቅም የሚገመግሙበትና ለዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የሚያቀርቡት አመታዊ ሪፖርት (SPAR 2025 ) አፈጻጸም የውይይት መድረክ የተካሄደ ሲሆን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ በመድረኩ እንደተናገሩት SPAR ለጤና ደህንነት በጣም አስፈላጊ ሲሆን መንግሥታትና የጤና ተቋማት የዝግጁነትና የምላሽ አቅም በግልጽ ሁኔታ እንዲያውቁ ያግዛል ብለዋል:: ፖሊሲዎችን፣ የሰው ኃይልን፣ የበሽታ የቅኝት ስርአቶች (surveillance) ፣ ላቦራቶሪዎችን እና የአደጋ ምላሽ ስርዓቶችን በመገምገም ክፍተቶችንና ጥንካሬዎችን መለየት እንደሚያስችል ገልጸዋል::
የብሔራዊ የጤና ደህንነት የድርጊት መርሀግብርም (NAPHS) ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ደህንነት ስርዓት፣ ከአለማቀፍ የጤና ደንብ ከ(IHR 2005) ጋር በሙሉ ለማጣጣም የተዘጋጀ ብሔራዊ የፖሊሲ መሣሪያ እንደሆነም ተናግረዋል::
ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ባለፉት ጊዜያት በNAPHS ትግበራ መሠረት በበሽታ ክትትልና መረጃ ስርዓት፣ በብሔራዊ እና ክልል ላቦራቶሪ ኔትወርክ፣ የድንበር ጤና ቁጥጥር እንዲሁም የጤና አደጋ ዝግጁነትና ምላሽ አቅም ላይ የሚታዩ እድገቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል:: የማርበርግ ቫይረስን በመቀልበስ ረገድ ለተገኘው ውጤትም የሕብረተሰብ ጤና ደህንነት ስራዎች የማይተካ ሚና እንደነበራቸው ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል::
የአገሪቱን ድንገተኛ የጤና አደጋዎች በፍጥነት የመለየት፣ የተቀናጀ ምላሽ እና የማስተዳደር አቅም በተግባር እያሻሻሉ መሆናቸውን የገለጹት ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በNAPHS ትግበራ ውስጥ በሳይንሳዊ ማስረጃ የተመሠረተ ውሳኔ መወሰንን ማጠናከር፣ የመረጃ ጥራትን በማሻሻል እና የተለያዩ ሴክተሮች መካከል ዘርፈ-ብዙ መተባበርን (Multisectoral Coordination) ማስፋት ላይ ያተኮረ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
የአንድ ጤና /One Heath/ እና የአለም ዓቀፍ የጤና ደንብ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ፈይሳ ረጋሳ በበኩላቸው የዓለም አቀፍ የጤና መመሪያ የተቀበሉ አባል አገሮች (States Parties) በየዓመቱ የራሳቸውን የጤና አቅም የሚገመግሙበትና ለዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የሚያቀርቡት አመታዊ ሪፖርት SPAR እና የብሄራዊ የጤና ደህንነት የድርጊት መርሀግብር (NAPHS) ትግበራ የአንድ ጤና (One Health) ምልከታን በተግባር ማስፈጸም ያስችላል ያሉ ሲሆን በሚቀጥሉት ጊዜያትም የNAPHS ትግበራን ማስፋት ላይ እና በSPAR የተያዙ 15 የእቅድ አመላካቾች ማለትም የበሽታዎች ቅኝት ፤ የምግብ ደህንነት ፤ ላብራቶሪ ፤ ተላላፊ በሽታዎች መለላከልና መቆጣጥር …ወዘተ ላይ ትኩረት እንደሚደረግ ገልጸዋል::
አባል አገሮች የበሽታ መከላከል፣ መቆጣጠር፣ መከታተልና መልስ መስጠት አቅማቸውን SPARE እንደሚረዳ የገለጹት ዶ/ር ፈይሳ በIHR (2005) መሠረት አገሮች የአፈጻጸማቸውን ሁኔታ በየዓመቱ ማሳወቅ ግዴታ እንዳለባቸውና ፤ SPAR ይህን ግዴታ ለመፈጸም ይጠቅማል ብለዋል:: የዓለም አቀፍ የጤና ደህንነትን ለማጠናከር እንዲሁም የSPAR ውጤቶች የጤና ፖሊሲ፣ ዕቅድና የሀብት አመዳደብን ለመሻሻል መሠረት እንደሚሆን ተናግረዋል::
በወርክሾፑ ከጤና ሚኒስቴር ፣ ከግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተመስሪያቤቶች ፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከመከላከያ ጤና መምሪያ፣ ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከዱር እንስሳት ባለስልጣን፣ የመጡ ባለድርሻዎች የተገናኙበት ሲሆን ከአጋሮችም የዓለም ጤና ድርጅት፣ የተባበሩት መንግስታት ምግብ እና እርሻ ድርጅት፣ የእንግሊዝ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ/ UKHSA/ ፣ሪዞልፍ ቱ ሴቭ ላይቭስ / RTSL/፣ ጂ ኤስ አይ/JSI/ ፣ ፕሮጀክት ሆፕ እና ኦሀዮ ስቴት ግሎባል ዋን ሄልዝ በአጋርነት ተሳትፈው መልእክትም አስተላልፈዋል::
ባስተላለፉት መልእክትም የዓለም ዓቀፍ የጤና ደንብን እና የብሄራዊ የጤና ደህንነት ስልታዊ እቅድን መሰረት አድርገው በአንድ ጤና ማእቀፍ በትብብር እና በቅንጅት ሲሰሩ እንደነበር ገልጸዋል:: በዚህም በሕብረተሰብ የጤና አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ፣ በሰው ኃይል እና በላብራቶሪ በአቅም ግንባታ፣ በግብዓት፣ በበጀት እና በሌሎች ቴክኒካል ስራዎች ድጋፍ ሲያደርጉ እንደነበር አውስተው ከወርክሾፑ የሚገኙ ግብዓቶችንም በመጠቀም በአንድ ጤና እሳቤ በትብብር እንደሚሰሩ አስረድተዋል::