የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ስራዎችን የሚያግዙ የሕክምና መሣሪያዎች ድጋፍ ተደረገ

September 20, 2025
የኦሀዬ ስቴት ዩኒቨርሲቲ (OSU) ከአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር (US CDC) ጋር በመተባበር ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተለያዩ በሽታዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተግባራት የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ድጋፍ አደረገ። ይህ ድጋፍ የተደረገው በUS CDC እና OSU መካከል በአለም ጤና ደህንነት ላይ የተደረገው ስምምነትን መሰረተ ያደረገ ነው።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መልካሙ አብቴ በርክክቡ ወቅት እንዳሉት US-CDC እና OSU በሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅኝት፣ መከላከል እና ምላሽ ላይ በምንራሰራቸው ስራዎች የረጅም ግዜ አጋሮቻችን እንደመሆናቸው አሁንም ያደረጉት ድጋፍ እነዚህን ስራዎቻችንን ቀጣይነት የሚደግፉ እና አቅማችንንም ለማጐልበት የሚያግዙ ናቸው።