የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብሔራዊ የስልጠና ማዕከል የ2014 በጀት ዓመት የሰባት ወር የስልጠና አፈጻጸም ሪፖርቱን በአዳማ ከተማ ሮቢ ሆቴል ለግምገማ እና ውይይት አቀረበ፡፡ ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር የውይይት መድረኩን በከፈቱበት ወቅት እንደገለጹት የስልጠና ማዕከሉ በበጀት ዓመቱ በዕቅድ በተመሰረተ ሁኔታ ወደ ስራ በመግባቱ አጥጋቢ የሆነ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉንና እንዲህ አይነት የውይይት […]