የክልሎች የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተሮች የኢንስቲትዩቱን የተለያዩ ክፍሎች ጉብኝት

September 2, 2026
የክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተሮች የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና የኢንስቲትዩትን የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ማስተባበሪያ ማዕከል (PHEOC)፣ የቫይራል ሄሞራጂክ ፊቨር (VHF) ላቦራቶሪ፣ የጂኖሚክስ ላቦራቶሪ እና የስነ ምግብ ላቦራቶሪዎችን የቴክኒክ ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝቱ ኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎችን በእውነተኛ ጊዜ ለማስተባበር፣ ከፍተኛ ስጋት ያላቸውን በሽታ አምጪ ተህዋስያን ለመመርመር፣ የጂኖም ክትትልና ትንተና ለማካሄድ እንዲሁም በስነ ምግብ ዘርፍ የላብራቶሪ ምርመራና ሳይንሳዊ ድጋፍ ለመስጠት ያለውን አቅም ለተሳታፊዎቹ እንዲያውቁ አስችሏል።