ሀገር አቀፉ የብሔራዊ የጤና ደህንነት መርሀ ግብር አፈጻጸም ስብሰባ ተከናወነ
በተቀናጀ እና በተናበበ መልኩ የሚከናወን ብሄራዊ የጤና ደህንነት መርሀ-ግብር ስኬታማ መሆን ለአጠቃላይ ሁለንተናዊ ለሆነው ሀገራዊ የጤና ድህንነት ስርአታችን አቅም መጎልበት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ፡፡
አቶ አስቻለው አባይነህ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዋና ዳይሬክተር በአዳማ ከተማ በተከናወነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጤና ደህንነት መርሀ ግብር አፈጻጸም የምክክር ስብሰባ ላይ በመገኘት ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ላይ እንዳስገነዘቡት ምንም እንኳን የሀገሪቱ የጤና ስጋቶችን የመከላከል፣ ሲከሰቱም ፈጥኖ የመለየትና አፋጣኝ ምላሽ የመስጠት አቅምን ለማጎልበት የሚረዱ ልዩ ልዩ መሠረታዊ የማስቻያ ሁኔታዎችን የተከናወኑ እና እየተከናወኑ ቢሆንም አሁንም ቢሆን የጤና ስርዓቱን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የሚረዱ ነገር ግን ያልተከናወኑ ቀሪ ተግባራት እና ሀገራዊ ፕሮግራሞችን በመፈጸምና በማስፈጸም ረገድ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር እንዲሁም ንቁ ተሳትፎና ርብርብን አስፈላጊ በመሆኑ ሁሉም ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
ምክትል ዳይሬክተሩ አያይዘውም የብሄራዊ ጤና ደህንነት መርሀ-ግብር ስኬታማ መሆን ለአጠቃላይ ሁለንተናዊ የጤና ድህንነት ስርአታችን አቅም መጎልበት ከፍተኛ እና በሁሉም የአስተዳደር እርከኖች ያሉ የጤና ስርአት መሻሻልና ለጤና ስጋቶች ያለንን ዝግጁነት፣ የመከላከል፣ የመለየትና ፈጥኖ ምላሽ የመስጠት ሁለንተናዊ አቅማችንን ለማጎልበት ከማስቻሉም በላይ ከራሳችን አልፎ ሀገራችን የፈረመችበትን የዓለም ጤና ዋስትና መረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ ለማበርከትና ብሄራዊ ግዴታችንን ለመወጣት ያስችለናል ብለዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ላይ ከልዩ ልዩ የመንግስት እና አጋር ተቋማት የተወከሉ ባለሙያዎች በስብሰባው መድረክ ላይ መገኘታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡