ሁለቱ ኢንስቲትዩቶች የጋራ የውይይት መድረክ አካሄዱ
November 22, 2023
የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (አህሪ) እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የስራ አመራሮች የጋራ ውይይት አካሄዱ፡፡
የሁለቱም ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ሀላፊዎች ህዳር 11/2016 ዓ.ም ያካሄዱት የውይይት መድረክ በጋራ ለመስራት የሚያስችሏቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡ በቀጣይ ለሚጠበቁብን ጥራታቸውን የጠበቁ የምርምር ስራዎችና ውጤቶች ላይ የሁለቱን ኢንስቲትዩቶች የጋራ ፍላጎትና ስራዎች በመለየት በትስስር ለመስራትና ያሉንን ሀገራዊ ሀብቶች ከድግግሞሽና ከአላስፈላጊ ወጪ ለመጠበቅና የሰው ሀይል ሀብቶቻችንን በጋራ መጠቀም የምንችልበትን አቅም ይፈጥርልናል ያሉት የአህሪ ዋና ዳይሬክተር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ ናቸው፡፡
በመድረኩ በሁለቱም በኩል የተዘጋጁ ገለፃዎች የቀረቡ ሲሆን በቀጣይ በተለዩና በትስስር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዩች ላይ ሰነድ ተዘጋጅቶ ግልጽ በሆነ ስምምነት አብሮነትን ፈጥሮ መስራት ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑንም የኢትዩጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ ገልፀዋል ፡፡
ውይይቱም በቀጣይ በተደራጀ መልኩ በየጊዜው እንደሚካሄድና በሁለቱ ተቋማት መካከል ያሉ ሰራተኞችን ማስተሳሰርና ያጋራ እሳቤ እንዲኖራቸው መሰራት ያስፈልጋልም ተብሏል፡፡