ለሀገር አቀፍ የምግብና ስነ-ምግብ ስትራቴጂ ጥናት የመረጃ ሰብሳቢዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው

ለሀገር አቀፍ የምግብና ስነ–ምግብ ስትራቴጂ ጥናት የመረጃ ሰብሳቢዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው
የኢንስቲትዩቱ የምግብ ሥነ መግብ ምርምር ዳይሬክቶሬት አገር አቀፍ የምግብና ሥነ ምግብ ስትራቴጂ መነሻ የሚሆን ዳሰሳ ጥናት (National Food and Nutrition Baseline Survey) ለማካሄድ የመረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጣሪዎችን ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ የኢንስቲትዩቱ ተወካይ ዋና ዳይሬክተር ስልጠናውን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ የጤና እና የስነ-ምግብ ዘርፎች ዙሪያ ምርምርና ሌሎች ስራዎች የሚሰራ ተቋም ከመሆኑ አንጻር ባለፉት ሁለት አስርተ አመታት ውስጥ የሕብረተሰባችንን ጤና ሲያቀውሱ እና በሃገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ አሉታዊ ተጸዕኖ ሲፈጥሩ የነበሩ የስነ-ምግብ ችግሮችን፣ እንደዚሁም የእናቶች እና ህጻናት ሞት ከመቀነስ አንጻር ብዙ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ እንዚህ የጤና ነክ ችግሮች መንስዔያቸው ተጠንቶ መረጃን አና ጥናትን መሰረት አደርጎ መፍትሄ መፈለግ ያስፈልጋል፡፡ ይህን መነሻ በማድረግ መነግስት የ10 ዓመት የምግብና የስነ-ምግብ ስተራቴጂ ማስተግበሪያ መመሪያ ማጽደቁ የሚታወቅ ሲሆን ለዚህም ስተራቴጂ ግብዓት የሚሆን የመነሻ የዳሰሳ ጥናትም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ የዳሰሳ ጥናት እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡
በመቀጠልም ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ የኢንስቲትዩቱ የምግብ ሥነ መግብ ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ስለ ምግብና ስነ-ምግብ ስትራቴጂ ጥናት ምንነት እና ከአሰልጣኞች እንዲሁም ከሰልጣኞች ምን እንደሚጠበቅ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
ጥናቱ ላይ ከተለያዩ ቡድኖች ማለትም ከምግብ ሳይንስ፣ ከስነምግብ፣ ከአከባቢ ሳይንስ ክፍልና ከላቦራቶሪ የተለያዩ ባለሙያዎች እንዲሁም ከክሊኒካሌ ላቦራቶሪና ከኢንፎሜሽን ቴክኖሎጂ የተውጣጡ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ሲሆን በአሁኑ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ላይ 170 መረጃ ሰብሳቢዎች እና ተቆጣጣሪዎች እንደሚሳተፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡