ለሐረሪና ድሬዳዋ ባለሙያዎች የተሰጠው የመስክ ኢፒዲሞሎጂ ስልጠና ተጠናቀቀ
ከሐረሪ እና ድሬዳዋ ለተውጣጡ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ባለሙያዎች የተሰጠው መሰረታዊ የመስክ ኤፒዲሞሎጂ ስልጠና ከሶስት ዙር ስልጠና በኋላ የተጠናቀቀ ሲሆን በዚህ ስልጠና በአጠቃላይ 38 በለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በስተመጨረሻም ላይ ሁሉም ሰልጣኞች በየምድብ ወረዳዎቻቸው የሰሩትን የጥናት ስራዎቻቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
አቶ ጃፈር ከዛሊ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል የዝግጁነትና የአቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ባለሙያ እና የስልጠናው አስተባባሪ እንደገለጹት ስልጠናው በሶስት ዙር የተሰጠ ሲሆን፤ ከመሰረታዊ የኮምፒውተር አውቀት፣ የበሽታ ቅኝት መረጃ እንዴት እንደሚሰባሰብ ማካታት ያለበትን እና ለሚመለከተው አካል እንዴት ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እንደሚቀርቡ እንዲሁም ወረርሽኝ ቢከሰት ምን መደረግ አለበት መንስዔውስ ምንድነው የሚለውን ጨምሮ በሶስቱ ዙር ስልጠናው ውስጥ የተካተቱ እንደነበር ጠቅለል አድርገው ያስረዱ ሲሆን ይህ ስልጠና ለነዚህ ከተሞች ሁለተኛ ዙር መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በስተመጨረሻም በስልጠናው ከፍተኛ ነጥብ ያመጡ ባለሙያዎች ከአቶ ኢብሳ ኢብራሂም የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ሃለፊ የምስክር ወረቀታቸውን የተቀበሉ ሲሆን በተጨማሪም ከዚህ በፊት ከሰልጣኞች ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ሶስቱም ተገቢውን ምላሽ እና አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡