ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
May 1, 2021
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁሉንም ሀገራት ያዳረሰ፤ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል የሚያጠቃ፤ለከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ እንዲሁም ለሞት የዳረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የስቅለት በዓልን ስናከብር ለስግደት ወደ ቤተ ክርስቲያን በምንሄድበት ወቅት የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን ማለትም:-
*ርቀትን መጠበቅ
*ማስክ ማድረግ
*የእጅን ንጽህና መጠበቅ
*ጉንፋን መሰል የህመም ስሜቶች እና ምልክቶች የሚያዩ ከሆነ እንዲሁም የኮቪድ-19 ቫይረስ ካለበት ሰዉ ጋር የቅርብ ንክኪ ከነበረዎት እራስዎን በመለየተ ምርመራ ማድረግ እና ፅሎትዎንና ስግደትዎን በቤት ውስጥ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኝ ግለሰብ፤ቤተሰብ፤መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤የሐይማኖት ተቋማት፣ሲቪክ ማህበራት፤አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤የጤና ባለሙያዎች፤መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ማስክ ማድረግ፣የእጃቸውን ንጽህና በተደጋጋሚ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ተገቢውን የጥንቃቄ መንገዶችን በመተግበር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚያደርሰውን ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች በጋራ እንድንከላከል የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥሪውን ያቀርባል፡፡
#መልካምየስቅለትበዓል
#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ
#COVID19Ethiopia
#NOMASKNOSERIVCE