ለኢትዮጵያ ሕብረተስብ ጤና ኢንስትቲዩት የማኔጅመት አባላት የአመራር ክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ነው
በሕብረተሰብ ጤና ዙሪያ የሚከናወኑ የአመራር ስራዎች በልዩ ልዩ ሙያዊ ስልጠናዎች መታገዛቸዉ የሚሰጠዉ ጠቀሜታ የላቀ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ከእንግሊዝ መንግስት የጤና ደህንነት ኤጀንሲ (UK-HAS) ጋር በመተባበር በቢሾፍቱ ከተማ እያከናወነ ባለዉ የኢትዮጵያ
ሕብረተስብ ጤና ኢንስትቲዩት የማናጅመንት አባላት የአመራር ክህሎት ስልጠና ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት
ዶ/ር መሳይ ሀይሉ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር እንዳስታወቁት አመራሮች የዕለት ተዕለት ስራቸዉን ይበልጥ ዉጤታማ በሆነ መንገድ
ለማከናወን ይቻላቸዉ ዘንድ ስራቸዉን የቃኘ እና ያገናዘበ መሰል ስልጠናዎች የሚሰጡት ጠቀሜታ የጎላ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
ዶ/ር መሳይ አያይዘዉም የሕብረተስብ ጤናው ዘርፍ የሚጠበቅበትን ሀላፊነትና ግዴታ በተቀናጀና ዉጤታማ በሆነ መልኩ መተግበር ይቻለዉ ዘንድ ሳይንሳዊ በሆነ
መንገድ መከተል ያለበትን የአመራር ክህሎቶች በማወቅና በመተግበር መንቀሳቀስ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ህብረተስ ጤና ኢንስትቲዩት ከእንግሊዝ መንግስት የጤና ደህንት ኤጀንሲ ጋር ያለዉን መልካም ግንኙነት ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚፈልግና አሁን በትብብር ከኤጀንሲው
ጋር እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ዋና ዳሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር ፒተር ሮቢንሰን የእንግሊዝ መንግስት የጤና ደህንነት ኤጀንሲ ምክትል ዳሬክተር በበኩላቸዉ ባደረጉት ንግግር መስርያ ቤታቸዉ ለኢትዮጵያ ህብረተስ ጤና ኢንስትቲዩት
እያደረገ ያለዉን የቴክኒክና የፋይናንስ እገዛ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚፈልግ ገልፀው ከዚህ የአመራር ክህሎትን ማዳበር ስልጠና የኢንስትቲዮቱ የማናጅሜንት አባላት
ጠቃሚ የሆነ ግንዛቤን እንደሚጨብጡ ተናግረዋል።
በቢሾፍቱ ከተማ ለአራት ተከታታይ ቀናቶች እየተከናወነ ያለዉ ይህ የአመራር ክህሎት የማጎልበቻ ስልጠና ከእንግሊዝ ሀገር በመጡ እና ለረዥም ዓመታት
በህብረተሰብ ጤናዉ ዘርፍ ልምድ ባካበቱ ባለሞያዎች በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡