ለኢንስቲትዩቱ ለግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

May 30, 2023
የኢንስቲትዩቱ የሰዉ ኃብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ለኢንስቲትዩቱ ለግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ሰራተኞች የዉስጥ ኦዲት አስፈላጊነትና ጠቀሜታ፣የስነ-ምግባር ምንነትና አስፈላጊነት፣የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ እና በሲቪል ሰርቪስ ደንብና መመሪያ ዙሪያ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ የመጀመሪያውን ዙር ስልጠና በአዳማ ከተማ ግንቦት 19/2015 ዓ.ም ሰጠ፡፡
እንደ ስልጠናው አስተባባሪዎች ስልጠናው በግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደቶች ላይ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍና የደንበኛ አገልግሎቶችን ለማሻሻል ያለመ ሲሆን በቀጣይ ዙርም ይንኑ ዓላማው በማድረግ ተመሳሳይ ስልጠና በተጠናከረ መልኩ ይሰጣል።