ለኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ
የኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ስጋት ተግባቦት እና የብረተሰብ ተሣትፎ የስራ ክፍል ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከተለያዩ ክልሎች ለተወጣጡ ለጤና፣ ለሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ስጋት ተግባቦት እና የህብረተሰብ ተሣትፎ ከመጋቢት 18 እስከ 20/ 2015 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ መሠረታዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡
የስልጠናው ዋና ዓለማ የፌደራል ፖሊስ የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ከሰራ ባህሪያቸው የተነሣ ለተለያዩ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ተጋላጭነታቸው የጐላ በመሆኑ ችግሮቹን በተሻለ መንገድ ለመቀነስ እንዲሁም የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ስጋት ተግባቦት እና የህብረተሰብ ተሣትፎ መረጃዎችን በተቋሙ በኩል በተናበበና ሣይንሣዊ በሆነ መንገድ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ነዉ።
አቶ ጀይላን አብዲ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ በስልጠናው ፕሮግራም ላይ ተገኝተው እንደገለጹት የካቪድ- 19 ወረርሽኝ በሐገራችን በተከስተ ወቅት የፌደራል ፖሊስ በከፍተኛ ደረጃ ኃላፊነቱን የተወጣ መሆኑን ጠቅሰው በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኩል ሲሰጥ የነበረው አሁንም እየተሰጠ ያለው የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ስጋት ተግባቦትና የሕብረተሰብ ተሣትፎ መሠረታዊ ስልጠና መረጃዎችን በተናበበና ሣይንሣዊ በሆነ መንገድ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ከመረግ አንፃር በባለሙያዎቹ በኩል ከፍተኛ ልውጥ የመጣ መሆኑን አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል::
ስልጠናው በሀገር አቀፍ ደረጀ ለተለያዩ ክልል የፌደራል ፖሊስ የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በዚህኛው ዙር ስልጠና 30 ለመሆኑ ለጤና፣ ለሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ስጋት ተግባቦት እና የህብረተሰብ ተሣትፎ መሰረታዊ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡