ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጤና ባለሙያዎች የአሰልጠኞች ስልጠና ተሰጠ
December 31, 2021
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የህብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል /EOC/ ለጤና አደጋ ስጋት ተግባቦት እና ለማህበረሰብ ተሣትፎ ለፌዴራል ፖሊስ ጤና ባለሙያዎች በሁለት ዙር ከታህሳስ 11 እስከ 22 /2014 ዓ.ም በድሬዳዋ እና በጅማ ከተማ የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ ።
የስልጠናው ዋና አላማ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መዋቅር ስር የሚገኙ የፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋማት እና የስምሪት ካምፓች የተሰማሩ የፖሊስ አባላት ከስራቸው አንፃር በካቪድ – 19 እና በሌሎችም የጤና አደጋ ወረርሽኞች ካላቸው ተጋላጭነት የተነሣ የመከላከል ስራዎችን ለማጠናከር የጤና ባለሙያዎችን የአሳልጠኞች ስልጠና በመስጠት በየተቋማቱ ለሚሰሩ የተለያዩ ሰራተኞች የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀ ነው።
ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች የተወጣጡ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ስር የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች በስልጠናው የተሳተፉ ሲሆን የጤና አደጋ ስጋት ተግባቦት ፣ የማህበረሰብ ተሣ ትፎ ፣ የመንግስት ተቋማት እና የሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የጤና አደጋ የሆኑትን ወረርሽኞችን እንዴት መከላከል እንደሚቻል የተሻለ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ስልጠና መሆኑን ስልጠናውን ሲሰጡ ከነበሩ ባለሙያዎች መረዳት ተችሏል ::