መርሆችና አሰራሮችን በመተግበር ሁላችንም የየበኩላችንን መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
December 19, 2022
አቶ አስቻለው አባይነህ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተዉ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ አዳዲስ ተነሳሽነት ያላቸውን መርሆችና አሰራሮችን በመተግበር ሁላችንም የየበኩላችንን መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
ም/ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ይህንንም እንዲረዳ ሁሉም አጋር ድርጅቶች በጋራ የሚሳተፉበትና የሚሰሩበት የባለሙያዎች ግብረ ኃይል ቡድንን ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይም በዋና ዋና ድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ፤ በኮቪድ -19 በሽታ፤ የሠብአዊ ምላሽ፤ በጤና ማዕከላት የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ስራዎችና ሌሎች ተያያዥ ርዕሰ ጉዱዮች ዙርያ በተከናወኑ ስራዎች ላይ ገለጻዎች ቀርበው ውይይቶች ተካሂዶባቸዋል።