ሴቶችን እናብቃ ልማትንና ሠላምን እናረጋግጥ
March 20, 2024
በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት “ሴቶችንእናብቃ ልማትንና ሠላምን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል በአለም ለ113ኛ በሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ለ48ኛ ጊዜየሚከበረውን የሴቶች ቀን በተለያዩ ፕሮግራሞች በኢንስቲትዩቱ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡
በክብረ በዓሉ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ፣ ዶ/ር ሳሮአብደላ እና ዶ/ር መልካሙ አብቴ እንዲሁም የዳይሬክቶሬት የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና የጤና ሚኒስቴር /የሴ/ማ/አ/ት/ስራአስፈፃሚ ወ/ሮ ፋጡማ ሰዒድ ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩም የተለያዩ አስተማሪ እና አዝናኝ ፕሮግራሞች ከመካሄዳቸው በተጨማሪ የሽልማትና የእዉቅና መስጫፕሮግራሞች ተካሂደዋል።