ስለ ጊኒ ዎርም በሽታ የግንዛቤ ማስጨበጫ አዉደ ጥናት በመካሄድ ላይ ይገኛል
July 7, 2023
የኢትዮጵያ የሕብረተሰ ጤና ኢንስቲትዩት ከካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለሚዲያ ባለሞያዎች ስለ ጊኒ ዎርም በሽታ ማጥፊያ ፕሮግራም አና በሽታው ያለበትን ሁኔታ ለማስገንዘብ እና የማሕበረሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ለማስቻል በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ ከሚድያ ባለሙያዎች ጋር የምክክር መድረክ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
የአዉደ ጥናቱ አላማ ስለ ጊኒ ዎርም በሽታ መልዕክት ማስተላለፍና ማሰራጨት፣ በሽታውን የማጥፋት መርሐ ግብር ላይ የሚዲያ ባለሞያዎች ተሟጋችነትና የአሸናፊነት ስሜት እንዲኖር እና በጊኒ ዎርም በሽታ ጉዳዮች ዙሪያ ሪፖርት ለማድረግና በሽታውን ለጠቆመ የሚሰጠው የገንዘብ ሽልማትን በአገር አቀፍ ደረጃ ለማሳደግና ተያያዥ ጉዳዮች ለመምከር ነው።
በመድረኩ ስለ ጊኒ ዋርም በሽታ ምልክት፣ስለ ሽልማቱ፣ስለ በሽታዉ አጠቃላይ መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ እና በሽታዉን እንዴት መጥፋት እንዳለበት ሰፋ ባለ መልኩ በፅሁፍ የተደገፈ ማብራሪያ እና ገለጻ ቀርቧል።
በአዉደ ጥናቱ ላይ የተለያዩ የሚዲያ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን በቀረቡ ገለጻዎች ላይ በመወያየት በቀጣይ በጋራ የሚሰራባቸው አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ።