ስነ-ምግባርንአስመልክቶስልጠናተሰጠ
የኢንስቲትዩቱ የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና መከታተያ ጽ/ቤት ስነ-ምግባርና ጸረ ሙስናን አስመልክቶ ለኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ከታህሳስ 25 እስከ 26 //2012 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ በቢን ሆቴል ስልጠና ሰጠ፡፡
የስልጠናው ዋና አላማ የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች በስነ-ምግባር የታነጻና የተመሰገኑ ሙስናን የሚጸየፍ ስራተኛ በኢንስቲትዩቱ ለመፍጠር ለሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሆኑን አቶ ፍፋ ዳባ የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና መከታተያ ጽ/ቤት ኃላፊ የስልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ተናግረዋል፡፡
ተገልጋዩ ህብረተሰቡ በኢንስቲትዩቱ የአገልግሎት አሰጣጥ ረክቶ፣ብልሹ አሰራንንና ሙስናን በማስወገድ ለሃገርና ለወገን የሚቆረቆር ሰረተኛ በኢንስቲትዩቱ ተፍጥሮ ማየት ጽ/ቤቱ በቀጣይ የሚጠብቃቸው ውጤቶች መሆናቸውን ሃላፊው አያይዘው ገልጸዋል፡፡
ማወቅና መተግበር ለስነ-ምግባር መሰረታዊ ጉዳዮች በመሆናቸው ስነ-ምግባርን በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል ፤በስነ-ምግባር የተገነባና የጎለበተ ሰራተኛ ደግሞ ጥራቱን የጠበቀ የመንግስት ስራ አገልግሎት መስጠት የሚችል ይሆናል፤ስለዚህ በሚገባ በስነ-ምግባር የታነጽን ልንሆን ይገባል፡፡ሲሉ አቶ አንተነህ ሃይሉ የፌዴራል የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ባለሙያ ስልጠናውን ለሰራተኛው በሚሰጡበት ወቅት ገልጸዋል፡፡
አቶ ሰለሞን ኃይለሚካኤል የፌዴራል የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ባለሙያ በበኩላቸው ሙስና ማለት የማይገባን ጥቅም አግባብነት በልሆነ መንገድ መጠቀም ማለት መሆኑንና ሙስና የሚለው ቃል በጣም ሰፊ እና ውስብስብ ከመሆኑም በላይ ኢ-ስነ-ምግባራዊ ተግባርና የወንጀል ድርጊት መሆኑን አብራርተው አስረድተዋል፡፡
የስነ-ምግባርን ምንነት፣የሙስና ጽንሰ ሃሳብ፣ሙስና በሃገር ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት እና የንብረት አያያዝና አስተዳደር በስልጠናው ወቅት ሰፊ ትኩረት የተሰጠባቸው ሲሆን በገለጻና በውይይት ስነ-ዘዴ ስልጠናው ሲሰጥ እንደ ነበር ተስተውሏል፡፡
ስልጠናው ወቅታዊ ፣እጅግ ጠቃሚና በርካታ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸውና በቀጣይ በግል ፣ በማህበራዊ እንዲሁም በተቋማቸው ለሚያድረጉት የተለያዩ እነንቅስቃሴ ላይ ስነ-ምግባርን ተላብሰው እንደሚሰሩ ስልጠናውን የወሰዱ ሰራተኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ስልጠናው በሁለት ዙር የተሰጠ ሲሆን በመጀመሪያው ዙር 66 የኢንስቲትዩቱ የሰራ ሃላፊዎች እና የቡድን አስተባባሪዎች ሲሆኑ በሁለተኛ ዙር ደግሞ ፣ የኢንስቲትዩ ጠቅላላ አገልግሎት፣የሰው ሃብት ስራ አመራር፣ግዥና ፋይናንስ፣የኢንስቲትዩቱ የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ፣ የሴቶችና ህጻናት ዳይሬክቶሬት ሰራተኞችን እና ሁሉንም የኢንስትዩቱን ዳይሬክቶሬትና ጽ/ቤት ጸሃፊዎችን ያካተተ ሲሆን በአጠቃላይ 124 የኢንስተትዩቱ ሰራተኞች በስልጠናወ ተሳትፈዋል፡፡