በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ የነበረዉ በአፈር ንክኪ የሚተላለፉ የአንጀት ጥገኛ ትላትሎች እና የብልሃርዚያ በሽታዎች የዳሰሳ ጥናት ዉጤት ይፋ ሆነ
በየኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የባክቴሪያል፣ፓራሲቲክ እና ዞኖቲክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬትከጤና ሚኒስቴር እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ የነበረው በአፈር እና በውሃ ንክኪ የሚተላለፉ የአንጀት ጥገኛ ትላትል /STH/ እና የብልሃርዚያ /SCH/ በሽታዎች ላይ ሲካሄድ የነበረው የዳሰሳ ጥናት ውጤት /national reassessment result dissemination / ከግንቦት 14 እስከ 16/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ጎልድን ቱልፕ ሆቴል በተካሄደው አዉደ ጥናት ይፋ ተደረገ።
በአዉደ ጥናቱ ማስጀመሪያ ስነ ስርአት ላይ የጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑትዶ/ር ሕይወት ሰለሞን ለአወደ ጥናቱ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ሲያስተላልፉ፣ የኢትዮጵያየሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ አዉደጥናቱን በይፋ ከፍተዋል።
አዉደ ጥናቱ የተካሄደዉ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ፣ ከጤና ሚኒስቴር የተለያዩ የትኩረት የሚሹ የሐሩራማበሽታዎች ባለድረሻ አካላት፣ ከThe END Fund፣ ከUnlimit Health፣ ከ ለንደን ስኩል ኦፋ ሀይጅን ና ትሮፒካል ሕክምናትምህርት ቤት፣ ከሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደር ተወካዮችና የተለያዩ የባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት ነዉ።
በዚህ አውደ ጥናት ላይ በበሽታዎቹ ዙሪያ በየክልሎች የተደረገዉ ዝርዘር ጥናታዊ ጽሁፍ በየኢትዮጵያ የሕብረተሰብጤና ኢንስቲትዩት ቀርቦ በሽታዎቹን ለመከላከልና መቆጣጠር ወደፊት መወሰድ ያለበት የህክምና ስትራቴጂ ሁሉምየክልል ጤና ቢሮዎች እንዲተገብሩ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም፣ በክልሎችና በጤና ሚኒስቴር ሲሰራ የነበረዉበሽታዎቹን የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ አበረታች መሆኑን ከአዉደጥናቱ ዉጤትና ከተሳታፊዎች አስተያየትለመረዳት ተችሏል፡፡
በአዉደ ጥናቱ ማጠቃለያ ላይ በየኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የባክቴሪያል ፣ፓራሲቲክ እና ዞኖቲክበሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይርክቴር የሆኑት ዶ/ር ገረመዉ ጣሰዉ እንደተናገሩት በአፈር ንክኪ የሚተላለፍ የአንጀት ጥገኛ ትላትል /STH/ እና የብልሃርዚያ /SCH/ በሽታዎችን ለመከላከል ለመቆጣጠርና ብሎም ለማጥፋት ለጤናሴክቴር ብቻ የሚተዉ ሥራ ሳይሆን የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍና ማህብረሰቡ የራሱን ጤና እራሱእንዲጠብቅና እንዲንከባከብ በማስተማርና በማስተባበርም ጭምር ነዉ ብለዋል። በማከልም በሽታዉን ለማጥፋትበሚደረገዉ ጥረት ዉስጥም የተሻለ የመመርመሪያ ዘዴ እንዲኖር በማድረግ በመረጃ ልዉዉጥ አጠቃቀምና አያያዝላይም የክልሎችን አቅም ማጎልበት አይተኬ ሚና ስላለዉ አጋር ድርጅቶች በዚህ ዙሪያም ድጋፋቸዉን መቀጠልእንዳለባቸዉ አሳስበዉ ለዚህ አዉደ ጥናት መሳካት አሰተዋጾ ያደረጉትን አጋር ድርጅቶች The End Fund, Unlimit Health, WHO, የጤና ሚኒስቴር አመራሮችና የስራ ክፍሎች የክልል ጤና ቢሮዎች የአወደ ጥናቱ ተሳታፊዎችና አሰተባበሪዎችንበማመስገን አወደ ጥናቱ ከሶስት ቀን ቆይታ በኃላ መጠናቀቁን አብስረዋል፡፡