በቀጣይ ሶስት ዓመታት በእናቶች እና ጨቅላ ሕፃናት ላይ የሚደረግ ጥናት ሊጀመር ነው
December 21, 2023
የኢንስቲትዩቱ የስርዓተ ጤናና ስነ-ተዋልዶ ምርምር ዳይሬክቶሬት በእናቶች እና የጨቅላ ሕፃናት የጤና ተደራሽነት፤ ፍትሃዊነትና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ የሚደረግ የሶስት ዓመታት ጥናት በኢንስቲትዩቱ የስልጠና ማዕከል የተለያዩ ኃላፊዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት ታህሳስ 10/2016 ዓ.ም የማስጀመሪያ አውደ ጥናት ተካሄደ
የጥናቱ ዋና ዋና አላማዎች ኢትዮጵያ በእናቶች እና የጨቅላ ሕፃናት ጤና ላይ የተመዘገቡ ተገቢ የጤና አገልግሎት/ክብካቤ/ ተደራሽነት፤ ፈትኃዊነት፤ የጤና አገልግሎት ጥራት እና የጤና ተቆማት የአገልግሎት ዝግጁነት፤ የጤናው ዘርፍ አፈጻፀም (efficiency) እና ፖሊሲዎች እንዲሁም ስትራቴጂዎች፤ አስቻይ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች በመተንተን የእናቶች እና የጨቅላ ሕፃናት ጤና በኢትዮጵያ ለማሻሻል በጥናት የተደገፉ ምክሮችን ለማቅረብ ያለመ ነው፡፡
በእናቶችና ጨቅላ ሕጻናት ጤና (በቅድመ ወሊድ፤ በወሊድና ድህረ ወሊድ የጤና አገልግሎቶች ላይ፣ በቤተሰብ ምጣኔ ፣ በህጻናት ክትባት እንዲሁም በሌሎች በጤና ሴክተሩ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጤና ጉዳዮች ላይ ጥናቱ ትኩረት እንደሚያደርግ ከአውደጥናቱ መረዳት ተችሏል፡፡