በትግራይ ክልል የተሰጠው የመሠረታዊ የፊልድ ኢፒዲምሎጂ ስልጠና ተጠናቀቀ
የኢትዬዽያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከትግራይ ክልል ለተውጣጡ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ባለሙያዎች ሲስጥ የነበረውን የመሠረታዊ የፊልድ ኢፒዲምሎጂ ስልጠና ተከታትለው ላጠናቀቁ ባለሙያዎች የካቲት 22/2016 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ የዕውቅና ስርተፍኬት ሰጠ።
አቶ አወል ዳውድ የስልጠናው አስተባባሪ ለዚህ ስልጠና ከተመዘገቡት ሠልጣኞች 28ቱ የሚጠበቅባቸውን የተለያዩ ስልጠናዎች እና የተሰጡ የተግባር ስራዎችን አጠናቀው ለዚህ ምርቃት በቅተዋል።
ይህ ስልጠና በክልሉ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ምክንያት ከተጀመረ በኋላ ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም አሁን እንደገና ተጀምሮ ለዚህ መብቃቱ ታላቅ ስኬት እንደሆነና ስልጣኞችም በክልሉ እየተከሰቱ ያሉ ወረርሽኞችን ለመከላከል ከስልጠናው ያገኙትን ዕውቀትና ልምድ ወደ ተግባር በማውረድ ሕብረተሰቡን ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው ያሳሰቡት የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ተወካይ አቶ መብርሀቶም ሀፍተ ናቸው።
የኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር የዝግጁነትና የአቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ መድሁኒዬ ሀብተፅዮን በአካባቢው የነበረውን የተለያዩ ችግሮች ተቋቁመው ለዚህ የበቁትን ባለሙያዎች እንኳን ደስ ያላቹህ ካሉ በኋላ ይህ የወስዱት ስልጠና ለቀጣይ የተለያዩ ስልጠናዎች ቅድሚያ እንደሚያገኙ ገልፀዋል።
ዶ/ር ፍስሃ በርሄ የኢንስቲትዩቱ የስልጠና ማዕከል አስተባባሪ በበኩላቸው የተከታታይ የባለሙያዎች ስልጠና (CPD) አካል ለሆነው የዚህ ስልጠና ተካፋይ መሆን ለሠልጣኞች የሚያስገኙትን ጥቅሞች በዝርዝር አስረድተዋል።