በትግራይ ክልል የኮሌራ በሽታ ክትባት ዘመቻ ተጀመረ
በትግራይ ከልል መቀሌ ከተማ በማይ ወይኒ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አቶ አስቻለው አባይነህ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ ዶ/ር ፋሲካ አምደስላሴ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጤና ቢሮ ሃላፊ፣ ዶ/ር ቦሬማ ሶምሞ የአለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር ጆይሲ ምፓያ የዩኒሴፍ የጤና ሴክሽኝ አስተባባሪ እንዲሁም የሌሎች አጋር ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል፡፡ ክትባቱ የክልሉን 13 ወረዳዎችን የሚያዳርስ ይሆናል፡፡
ከማስጀመሪያ ሥነ ስርዓቱ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ የተሰጠ ሲሆን አጠቃላይ በአሁኑ ወቅት ኮሌራን አስመልክቶ ያለውን ሁኔታ አቶ አስቻለው አባይነህ የሚከተለውን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
እንደሚታወቀዉ የኮሌራ ወረርሽኝ በሀገሪቱ የተለያዩ የአገራችን ስፍራዎች የተከሰተ መሆኑ እና የአገራችን ዋናኛ የህብረተሰብ ጤና ችግር መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑንም ከ2008 እስከ 2013 ዓ.ም. ውስጥ በድምሩ 19,844 የኮሌራ ታማሚዎች እና 327 ሞት (1.6% የሞት መጠን) የተከሰተ ሲሆን በ2013 ዓ.ም. ብቻ በሀገራችን 1758 የኮሌራ ታማሚዎች እና 23 ሞት (1.3% የሞት መጠን) የተከሰተ ሲሆን በአሁኑ ሰአት በተሰራዉ ሰርፈ ብዙ ስራ በአገራችን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ተችላል፡፡ በትግራይ ክልል ከ2008-2012 ባሉት አራት ዓመታት ዉስጥ በኮሌራ በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 6,699 ሲሆን 66 ሞት (0.99% የሞት መጠን) ሊከሰት ችሏል፡፡ በ2013 በጀት ዓመት በትግራይ ክልል የኮሌራ ወረርሽን ያልተከሰተ መሆኑ ሉን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ባለፉት ዓመታት እና በያዝነው 2013 በጀት ዓመት የኮሌራ ወረርሽኝ ክስተትን ለመከላከልና መቆጣጠር የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛል፡፡ ከነዚህም መከላከልና መቆጣጠር ስራዎች መካከል ለምሳሌ፡- አስፈላጊዉ የወረርሽን ግብአቶችን ክትባትን ጨምሮ ማሰራጨት፣ የተጠናቀረ ቅኝት በመዘረጋት የመረጃ ልዉዉጥን በማጠከር የኮሌራ ወረርሽኝን መከላከል፣ ወረርሽኙ በተከሰተባቸዉ ቦታዎች ሞት እነደሰይከሰት ጥራት ያለዉ ህክምና መስጠት የተጠናከረ ተግባቦት፣የጤና ትምህርት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መስራት በዚህ አመት የኮሌራን ወረርኝ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በአጠቃላይ 239 የኮሌራ ሕክምና ማዕከል ድኝኳኖች (CTC kit) የተሰጩ ሲሆን ወደ 2,192 የዉሃ ማጠራቀሚያ ታንከር እና 537,648,973 የተለያዩ የዉኃ ማጣሪያ ኬሚካሎች መሰራጨታቸዉ እና የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
በትግራይ ክልል የኮሌራ በሽታ እነዳይገባ ስጋቶችን የመለየት እና ቅድመ መከላከል ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ከዚህም ዋናኛዉ የግል እና አአካባበቢ ንጽህናን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ግብአቶችን መማላት ነዉ፡፡ ከዚህም አንጻር በርካታ የዉሃ ማከመያ ግብአቶች አና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች የተሰራጩ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም 11 የኮሌራ ማከሚያ ኪት ለትግራይ ክልል የተሰራጨ ሲሆን 5 ኪት ወደ ሽሬ ዙሪያ አካባቢ እና 6 ኪት ደግሞ በክልል ደረጃ ተሰራችታል፡፡ የኮሌራ ወረርሽኝ ክስተትን ለመከላከልና መቆጣጠር ከምንጠቀምባቸዉ ዋና ዋና መንገዶች መካከል የኮሌራ ክትባት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ2011 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በስድስት ክልሎች (አ.አ. ፣ ኦሮሚያ ፣ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሲዳማ ፣ ሶማሌ እና ጋምቤላ) ክልሎች በተመረጡ 45 ወረዳዎች ዉስጥ ከ1 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ 4 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ተከትቧል፡፡ ክትባቱ በታቀደ መልኩ የተሰጠ ሲሆን በአማካይ 99.5% አፈፃፀም የተገኘ ሲሆን ወረርሽኙ በተደጋጋሚ የሚያጠቃቸዉ ቦታዎች ክትባቱ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ባለዉ ጊዜ ድረስ ወረዳዎቹ ከወረርሽኙ ነፃ በመሆናቸዉ ክትባቱ ያመጣዉ እምርታ እጅግ በጣም ጥሩ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ የኮሌራ ወረርሽኝ ክስተትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሀገሪቱ ያሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የጋራ ርብርብ እጅግ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ እና ስራዉ ቀጣይነት እንዲኖርው በተጨማሪም ደግሞ የዓለም አቀፍ ኮሌራ ፍኖተ-ካርታ 2030 (Global cholera road map, 2030) በኮሌራ ምክንያት የሞትን መጠን በ90% ለመቀነስ በሚለዉ ግብ መሰረት ሀገራዊ ኮሌራ እቅድ 2014-2021 (National Cholera Plan/ NCP, 2021-2028) የቀጣይ 8 ዓመት ሰነድ ተዘጋጅቶ በአለም አቀፉ የኮሌራ መቆጣጠር ግብረ-ኃይል (Global Task-Force for Cholera Control, GTFCC) ሰነዱን ለማፅደቅ በውይይት ላይ ይገኛል፡ ፡ በትግራይ ክልል የአሁኑን ወቅታዊ እና ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የኮሌራ ወረርሽኝ ሊከሰት ይችላል ተብሎ በሚገመቱ የተመረጡ 13 ወረዳዎች ወስጥ ላሉ ክሁለት ሚሊዮን ህዝብ በላይ የተፈናቃይ ሰፈራ ቦታዎች እና ከ1 ዓመት ዕድሜ በላይ ለሆኑ ለሁሉም ተጋላጭ የሕብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱ ከሰኔ 3-9/ 2013 ዓ.ም እተሰጠ የሚገኝ ሲሆን በዛሬዉ እለትም በመቀሌ አካባቢ ክትባቱን በይፋ አስጀምረናል፡፡ ክትባቱ በሁለት ዙር የሚሰጥ ሲሆን ሁሉም በመጀመሪያ ዙር የተከተቡ ሰዎች ሁለተኛዉን ዙር የክትባት ዘመቻ ከመጀመሪያዉ ዙር ከ2 ሳምንት በኋላ እስከ 1 ወር ጊዜ ዉስጥ መከተብ ይኖርባቸዋል፡፡ ስለዚህ ህብረተሰቡ ክትባቱን በንቃት ተከታትሎ እንዲከተብ በአደራ ጭምር እናሳስባለን፡፡ በአጠቃላይ ለክትባት ዘመቻዉ ስኬት ይረዳ ዘንድ ሁሉም የሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት፣ አጋር ድርጅቶች እና የፀጥታ አካላቶች የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ ጥሪ እያቀረብን ህብረተሰቡም ኮሌራን በዘላቂነት ለመከላከል ክትባቱ ብቻ በቂ ስላልሆን ሌሎችን የመከላከያ ተግባራት ማለትም የግል እና የአካባቢ ንጽህና መጠበቅ፣ምግብን አብስሎ መመገብ፣በተቻለ መጠን ለመጠጥ የሚዉል ዉሃን አፍልቶ እና አቀዝቅዞ (ወይም በኬሚካል አክሞ መጠቀም) ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ እያሳሰብም ለዚህ ምላሽ ስራዎች መሳካት አስፈላጊዉን አስተዋጾ ያደረጉ የአለም ጤና ድርጅት፣ ዩኒሴፍእንዲሁም ሌሎች አጋሮች እና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከፌዴራል ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ድጋፍ ላደረጉ በሳለሙያዎች በኢንስቲትቱ እና በጤና ሚኒስቴር ስም ምስጋናዮን አቀርባለሁ በማለት መግለጫቸውን አጠናቀዋል፡፡