በአርባምንጭ ከተማ ለክልሉ የመጀመሪያ የሆነው የኢንፍሎዌንዛ ላቦራቶሪ በይፋ ተመረቀ።
በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል አርባምንጭ ከተማ ውስጥ የሚገኘውን እና በ CARES Act Project እገዛ የተገነባውን የኢንፍሎዌንዛ ላቦራቶሪ የክልሉ የጤና ቢሮ፣
የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የዞን አስተዳደር፣ የዞን ጤና መምሪያ እና የአጋር አካላት ኃላፊዎች እና አመራሮች በተገኙበት በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
ይህ ላቦራቶሪ ሀገር አቀፉን የኢንፍሉዌንዛ ማዕከል አቅም ይበልጥ ለማጎልበት ከተገነቡት አራት የክልል የኢንፍሎዌንዛ ላብራቶሪዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን ላቦራቶሪዎቹን
በመገንባትና በግብአቶች በማሟላት እንዲሁም በኮቪድ -19 ቅኝት እና ላብራቶሪዎች ሥርዓት በማስተባበርና በማሳለጥ በኩል CARES Act Project ከፍተኛ እገዛ አድርጓል።
በምርቃት መርሃግብሩ የተገኙት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምዋና ዳይሬክተር እንደተናገሩት ይህ የምርመራ ላቦራቶሪ የክልሉን የላቦራቶሪ
የመመርመር አቅም ይበልጥ የሚያጠናክር እና የኢንፍሎዌንዛ አይነትና ሌሎች የመተንፈሻ አካል የምርመራ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ነው፡፡ ድንገተኛ በሽታዎች ሲከሰቱ ቀድሞ
በመለየት እና ለሚሰጠው ምላሽም ግብአትን በማቀበል ረገድ ላቦራቶሪው የማይተካ ሚናን ይጫወታል፡፡
በመቀጠልም ሁሌም እገዛና ድጋፍ ለሚያደርጉት የኢንስቲትዩቱ አጋሮች Ohio State University- Global One Health Initiative
(OSU-GOHi) እና US- Centers for Disease Control and Prevention (US-CDC) እንዲሁም በCARES Act Project ድጋፍ በኩል ለተከናወነው ታላቅ ስራ፤ እገዛና ያልተቆጠበ ድጋፍ ሲያደርጉ ለነበሩ የሀገር አቀፍና የክልል የበላይ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።