በኢትዮዽያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጀመረ።
የኢትዮዽያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎትን ያስጀመረ ሲሆን በዚህ የክረምት የበጎ ፍቃድ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ እንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ ከያዛቸዉ የክረምት በጎ አድራጎት እቅዶች መካከል የደም ልገሳ፣ለአቅመ ደካሞች ቤት እደሳ እና የነፃ የላቦራቶሪ ምርመራ ስራዎች ይገኙበታል።
ዶ/ር ጌታቸው አያይዘውም የላቦራቶሪ አገልግሎቶቹ ለማንኛዉም የማህበረሰብ ክፍል እንደሚሰጥ ጠቁመው በዋናነት ትኩረት የሚያደርገዉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ሲሆን ይህም የነጻ አገልግሎት እስከ ጳጉሜ 5/2015 የሚሰጥ ሲሆን አገልግሎቱንም ከ5000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች እንደሚዳረስ ይጠበቃል
ከዚህ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አንድ አካል የሆነው ለአቅመ ደካሞች ቤት የማደስ መርሀ ግብርም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር የአስተዳደሩ አመራሮች በተገኙበት ም/ል ዋና ዳይሬክተሩ አስጀምረዋል።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ በዚህ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ እንደገለጹት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባር እንቅስቃሴ በማጠናከር ኢንስቲትዩቱ ከዚህ ቀደም የትምህርት ጥራት በማስጠበቅ በተሻለ መልኩ በመስራት ንፅህናው የተጠበቀ ዉሃ እና መፀዳጃ ቤቶች ለተለያዩ ትምህርት ቤቶች፣ 200 ለሚሆኑ ተማሪዎች ደብተር እርሳስ እክርቢቶ ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት እንደ ሀገር ክቡር በጠቅላይ ሚኒስቴር የተጀመረዉ የክረምት በጎ አድራጎት ስራዎች ዉስጥ እንዱ እና ዋነኛው ዕርዳታ ሚፈልጉ የማህበረሰብ አካል የሆነዉ በክረምት ጎርፍ ዉሃ እየገባባቸዉ የሚቸገሩ ንፅህናቸዉ ያልተጠበቁ ቤቶች ፈርሰዉ አንደገና ምቹ በሆን መልኩ ተገንብተዉ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረው ይህንንም ለመተግበር ኢንስቲትዩቱ የሚገባውን እየተወጣ እንደሚገኝ አብራርተዋል።