በኢትዮጵያ አስተማማኝ እና ወቅቱን የጠበቀ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መረጃ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚሰጥ ዲጂታል ፕላትፎርም በይፋ ሥራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ – ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም. – የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና
ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን በአምስት የተለያዩ ቋንቋዎች ለህብረተሰቡ ዘላቂ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መረጃ የሚሰጥ ዲጂታል አገልግሎት በዛሬው ዕለት በይፋ ሥራ አስጀመሩ።
8335 በመባል የሚታወቀው እና በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና በማስተርካርድ ፋውንዴሽን የተዘጋጀው ይህ ዲጂታል ፕላትፎርም እንደ ኮቪድ-19፣ ቢጫ ወባ፣ ኮሌራ እና ጊኒ
ወርም ባሉ በሽታዎች ዙሪያ የህብረተሰብ ጤና አደጋ መረጃዎችን የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ ህብረተሰቡ እንዲያውቀው እና አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስድ ሲባል ከቅርብ
ጊዜ ወዲህ የተከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ወረርሽኝም የመረጃ ሥርዓቱ ውስጥ ተካቷል። ፕላትፎርሙ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች የተፈናቀሉ ሰዎች አስፈላጊ የሆኑ የጤና መረጃዎችን
ቀልጣፋ በሆነ መልኩ እንዲያገኙ ይረዳል።
ነባሩ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መረጃ ማዕከል ያለው አቅም በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር የተደረገ በመሆኑ አገልግሎቱ በጀመረ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥም 100ሺ በላይ ለሚደርሱ
መረጃ ጠያቂዎች በተጠቀሱት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ዙሪያ መረጃ ማድረስ የተቻለ ሲሆን በጠቅላላ 300ሺ ጥሪዎችን አስተናግደዋል። የዲጂታል ፕላትፎርም በተለያየ ወቅት በልዩ
ልዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሊከሰቱ የሚችሉ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችንም ከህብረተሰቡ ጥቆማ መቀበል የሚያስችል አሰራር ያለው በመሆኑ ብሔራዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ
መረጃ ማዕከሉ አስተማማኝ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ እና የቅድመ ልየታ ወይም ቅኝት ምንጭ እንዲሆንም ያስችለዋል። ብዛት ያለው የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚያዳርስ
የሕብረተሰብ ጤና አደጋመረጃ መስጠት በሚያስፈልግበት ጊዜ በአጭር ጊዜ ውስጥ በድምጽና በአጭር የጽሁፍ መልእክት ማስተላለፍ የሚያስችል ነው፡፡ የልዩ ባለሙያ መልስ
የሚሹ ጥያቀዎችን በመቀበል በዘርፉ ልዩ ባለሙያ በሆኑት ምላሽ ለጠያቅው ማስቅመጥ የሚያስችልም ፕላትፎርም ነው፡፡ ይህ ፕላትፎርም እንደአስፈላጊነቱ ለተመረጡ አካላት
የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መረጃ መስጠት ወይም መቀበል የሚያስችልም ነዉ።
ሥርዓቱ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት ያላትን የጤና ሥርዓት በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሻሽል ነው። ፕላትፎርሙ እንደ የኮቪድ-19 የመረጃ ቋት እና ዲስትሪክት ሄልዝ ኢንፎርሜሽን
ሲስተም 2 (District Health Information System 2) እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው የመረጃ ሥርዓቶች መረጃ ይሰጣል እንዲሁም ይቀበላል።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር እና ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ፕላትፎርሙን በማሻሻል ጊዜውን የጠበቀ እና አስተማማኝ
የህብረተሰብ ጤና አደጋ መረጃ መስጠቱን ይቀጥላል።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሃይሉ እንዳሉት “የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መረጃ ማዕከሉ ኮቪድ-19ን ጨምሮ
ከአራት የሕብረተሰብ ጤና ስጋቶች ጋር የተያያዙ መሰረታዊ መረጃዎችን ዲጂታል በሆነ መልኩ አቀናጅቶ በማቅረብ አገልግሎት ይሰጣል እንዲሁም
ከሕብረተሰቡ ጥቆማዎችን ይቀበላል። በተጨማሪም መረጃዎቹ
በተለያዩ ቋንዎች የሚሰጡ መሆናቸው እነዚህን አገልግሎቶች ማግኘት ለሚፈልጉ በአንጻሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ይበልጥ ተደራሽ ያደርጋቸዋል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ሚ/ር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በበኩላቸው
“ዲጂታል ቴክኖሎጂው የጤና መረጃ ከመስጠት በተጨማሪ በአሳታፊ የድምጽ ምልልስ (IVR) አማካኝነት በተደጋጋሚ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።
ይህም “የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መረጃ ማዕከሉ የጤና ባለሞያዎች ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚወስዱትን ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንስ ነው። ሥርዓቱ መልዕክቶችን
በፍጥነት የሚቀበል እና የሚያደርስ መሆኑ የመረጃ አቅርቦቱ ይበልጥ ቀልጣፋ እና ቀላል በሆነ መልኩ እንዲከናወን ያስችላል” በማለት አክለዋል።
በተጨማሪም የማስተርካርድ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሳሙኤል ያለው አደላ “በ2012 ዓ.ም. የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበት
ወቅት በኢትዮጵያ የሚገኘው ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ወረርሽኙ የሚያስከትላቸውን ተግዳሮቶች ለመፍታት በሀገር ደረጃ በርካታ ሥራዎችን ሠርቶ ነበር።
ይህ አዲስ ዲጂታል አገልግሎትም ህዝቡ ስለጤናው መረጃን መሰረት ያደረጉ ውሳኔዎችን እንዲወስን የሚያስችል ይሆናል። በተጨማሪም ከዚህ ዲጂታል
ፕላትፎርም የሚገኙት ትምህርቶች የተለያዩ ዘርፎች ላይ ለምንሰራው ዲጂታል ሥራ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ይሆናሉ። የቴክኖሎጂ ኃይልን በመጠቀም
በመላው ኢትዮጵያ ቅልጥፍናን እና ግንኙነትን ማሳደግ የሚለውን ግብ ዕውን እናደርጋለን” ብለዋል።