በኢንስቲትዩቱ የSORT IT ስልጠና መካሄድ ጀመረ
በዓለም ጤና ድርጅት አማካኝነት የሚሰጠው SORT IT (Structural Operational Research and Training Initiative) ስልጠና ትኩረት ያልተሰጣቸው በሽታዎች (Neglected Tropical Diseases) ላይ መሰረት በማድረግ የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ለማበረታታት የሚሰጥ የስልጠና ዓይነት ሲሆን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የብሔራዊ የስልጠና ማዕከል ከዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት ጋር በመተባበር ከኢንስቲትዩቱ ጥናትና ምርምር ባለሞያዎችና በኢትዮዽያ ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ተመራማሪዎችን ያካተተ ነው፡፡
ስልጠናው በኢንሰቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ ጥቅምት 12/2016 ዓ.ም በይፋ የተከፈተ ሲሆን ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም ስልጠናው ከዓለም የጤና ድርጅት ጋር በመተባበር የሚሰጥ መሆኑንና በዘርፉ ላሉ ባለሙያዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የገለፁ ሲሆን የዓለም የጤና ድርጅት የስልጠና እና የምርምር ፕሮግራም ዘርፍ ሀላፊ ዶ/ር ሮበርት በበኩላቸው ስልጠናው በምረምሩ ዘርፍ ያለውን ጠቀሜታም እናም ስልጠናውን ለመስጠት የተለያዩ ከፍተኛ ተመራማሪዎች ከአውሮፓ እና ከእንግሊዝ ሀገር መገኘታቸውን አብራርተዉ ገልፀዋል፡፡
የስልጠና ማዕከሉ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሀመድ አህመድ እንደገለፁት የዓለም ጤና ድርጅት በተለያዩ ሀገራት የስልጠና ፕሮግራም ያሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ የኢትዮጲያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ስልጠና ማዕከል አንዱ እንዲሆን እየተሰራ ሲሆን ስልጠናው በጥናትና ምርምር ዘርፍ የተመረጡ ተመራማሪዎች ትልቅ አቅም እንደሚሰጥ እና በቀጣይነትም ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡
በመጨረሽም የኢትዮዽያ የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ተወካይ ከኢንስቲትዩቱ የስልጠና ማዕከል ጋር በቀጣይነት በቅንጀት ለመስራት ይህ ለዚህ ለኢትዮጵያ ተመራማሪዎች ጠቃሚ ልሆነ ፕሮግራም ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ሲሆን በመቀጠል ሌሎች የአቅም ግንባታ ሥራዎች በማቀናጀት እንዲሚፈጸም አሰረድተዋል፡፡
ስልጠናው ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን ከ10 በላይ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ቀርበው ውይይትም እንደሚደረግባቸው ታውቋል፡፡