በኢንስቲትዩቱ ጉብኝት ተካሄደ
October 15, 2019
21ኛውን የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የጤና ሚኒስቴር ዴኤታዎች፣ ከተለያዩ ክልሎች የመጡ የጤና ባለሙያዎች የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ሃላፊዎች በተገኙበት ጥቅምት 3/2012 ዓ.ም የኢንስቲትዩቱን የተለያዩ የምርምር ላቡራቶሪ ክፍሎችን ጉብኝት አደረጉ፡፡
ለጉብኝዎች ባለሙያዎች ስለ ኢንስቴትዩቱ አመሰራረት ታሪካዊ ዳራና ፣አሁን ያለበትን ደረጃ እንዲሁም በቀጣይ ሊደርስበት ስላለው ግብ አጠቃላይ ምን እንደሚመስል አቶ ጎንፋ አያና ከኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ጉብኝቱ የተካሔደው በ7 ቡድን በመክፈል ሲሆን ክትባትና ምርት ዳይግኖስቲክስ ፣ ባህል እና ዘመናዊ ምርምር ፣ የምግብ ሳይንስ ምርምር ፣ባክቶሮሎጂ፣ ኤቸ አይ ቪ እና ቲቢ ዳይሬክቶሬት ስር የሚገኙ በአጠቃላይ 7 ላቡራቶሪዎች ተጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ከባለሙያዎቹ የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮችም ላይ የተለያዩ ደጋፊ አስተያየቶችን ሰጥተዋል ፡፡
ከጥቅምት 4 እስከ 7/2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ በእስካይላይት ሆቴል በሚካሄደው ዓመታዊ የጤና ዘርፍ ጉባኤ ላይ ኢንስቲትዩቱ የተለያዩ የኤግዚብሽን ዝግጅቶችን በመያዝ የሚሳተፍ ይሆናል፡፡