በኤች ኤይቪ ላይ የሚደረገዉ ምላሽ ይበልጥ ዉጤታማ ይሆን ዘንድ በመረጃ ላይ የተደገፉ ልዩ ልዩ የጥናት ሥራዎች የሚሠጡት ጠቀሜታ እጅግ የጐላ እንደሆነ ተገለፀ

በዛሬዉ እለት የጤና ሚኒስቴር ፣የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት፣ ሁሉም የክልል ጤና ቢሮዎች እና አጋር አካላት በተገኙበት በተከናወነዉ አዉደ ጥናት ላይ እንደተገለፀዉ የሁሉም አካላት ተቀናጅቶና ተባብሮ መስራት ያለዉ ጤቀሜታ የጐላ እንዲሆን ተብራርቶል፡፡
በጤና ሚኒስቴር የኤች አይቪ ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ ምርቴ ጌታቸዉ በአዉደ ጥናቱ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር እንዳስገነዘቡት ሁሉም አጋር ድርጅቶች እገዛና ትብብር በተደረገዉ እልህ አስጨራሽ ርብርብ በአሁን ወቅት በኤድስ ምክንያት የሚከሰት ሞት የቀነሰ ቢሆንም በአንዳንድ ቦታዎች የበሽታዉ ስራዎች ከፍተኛ የሆነባቸዉ ቦታዎች ስላሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረዉ መቀጠል እንዳለባቸዉ አሳስበዋል፡፡
አስተባባሪው አክለዉ የዓለም ጤና ድርጅት ለየሀገሪቱ በየጊዜዉ እንዲተገበሩት ከሚያወጣቸዉ አዳዲስ አሰራሮች መካከል አንዱ ሆኖ ጥራት፣ ወቅታዊ ታማኝነት ያለዉ መረጃ ለማህበረሰቡ ማድረስ በመሆኑ ይህ አዉደ ጥናት መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡በመሆኑም ሀገራችን የኤች አይቪ ቀኝትን እ.ኤ.አ ከ2014 ጀምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ በ400 ጤና ተቆማት በመተግበር ላይ ይገኛል ፡፡
የሲዲሲ ኢትዮጵያ ተወካይ የሆኑት ዶ/ር አሸንፊ ሀይሌ በበኩላቸዉ ሲዲሲ ኢትዮጵያ ኤች ኤይቪ በሽታ በመከላከል ስራ ላይ ከመጀመሪያዉ ጊዜ ጀምሮ ንቁ ተሳትፎ እንደነበረዉ አዉስተዉ አሁንም ሆነ ወደ ፊት ተቆማችን በሚደረጉ መሰል ስራዎች ጋር ከመንግስት ጋር በመቀናጀት ለመስራት ቁርጠኛ አቆም እንዳለቸዉ አስታዉቀዋል፡፡
ፕሮፊሰር ስለሺ ልዑልሰገድ የአይካፕ ኢትዮጵያ ተወካይ በበኩላቸዉ ኤች ኤይቪ በሽታ ከመከላከል አንፃር በርካታ ለዉጦች መመዝገባቸዉ አዉስተዉ በተለይ በአሁኑ ወቀት በዳታ (መረጃ) ላይ በመመርኮዝ የሚከናወኑ ስራዎች እየጎለበቱ መምጣታቸዉ ብሎም መረጃ የመጠቀም ባህሉ መጎልበቱ ለሚከናወኑ ስራዎች ዉጤታማነት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለዉ አስረድተዉ ተቆማት በጋራ የሚያደርጉትን ቅንጅታዊ ስራ አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡