በወባ፣ በኮቪድ 19 እና የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታዎች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፡፡

14 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገራት ላይ እየጨመረ ባለው የወባ በሽታ እየተጠቁ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት እንደሚያሳይ የገለፁት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ
ሀምሳ ሁለት በመቶ በላይ የሚሆነው የሀገራችን ቦታዎች ላይም ችግሩ እንዳለ ገልፀዋል፡፡ ይህም ችግር እየጨመረ ለመምጣቱ እንደምክንያት የሚጠቀሰው ምቹ የአየር ንብረት መኖሩ፣ በሀገራችን ያለው የፀጥታ ሁኔታ ችግሮቹ
ባሉበት ቦታ ላይ የመከላከል ስራን ለማከናወን እንቅፋት መኖሩን፣
የአልጋ አጎበር አጠቃቀም ላይ የግንዛቤ እጥረት በመኖሩ እና ለተለያዩ የልማት ስራዎች ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጁ የውሃ ማቆር ለችግሩ መስፋፋት አይነተኛ ምክንያት ነው
ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም ችግር ምላሽ ለመስጠት የሚከናወኑ ተግባራት እንዳሉ ገልጸው በየሳምንቱ ከክልሎችና ወረዳዎች ሙሉ መረጃ በማምጣት፣ ከፍተኝ የህሙማን ባሉበት ቦታ ላይ
የቴክሊክ ድጋፍ በማድረግ፣ 5.5 ሚሊዮን የሚሆን የምርመራ መሳሪያዎችን በየክልሉ ድጋፍ በማድረግ እና በተጨማሪም የፀረ ወባ መድሀኒት በማሰራጨት በሽታውን የመካላከል ስራዎች
እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አክለውም 2.9 ሚሊዮን አጎበር ስርጭት በየክልሉ ማድረግና 1.6 ሚሊዮን በላይ የፀረ ወባ ርጭት ለማድረግ መታሰቡን ዶክተር ደረጀ አስታውቀዋል፡፡
በሌላ በኩል የኮቪድ 19 በሽታ ቀደም ሲል ይታይ ከነበረው ጫና አሁን የቀነሰ የመጣ ቢሆንም በማህበረሰቡ ያለው መዘናጋት ምክንያት ተመልሶ የማንሰራራትና የመጨመር ሁኔታ ይታያል ብለዋል፡፡ ይህንንም ስጋት ለመቀነስ ሁሉም ማህበረሰብና ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ ሁኔታ ርብርብ ማድረግና ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በአሁኑ
ጊዜ ሶስተኛው ዙር የኮቪድ 19 መከላካያ ክትባት እየተሰጠ በመሆኑ ያልተከተቡ ሰዎች መከተብ እንዳለባቸውና የተከተቡም ቡስተር ዶዝ መውሰድ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በመቀጠልም በዓለም ላይ ስጋት የሆነው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ በሀገራችን የተያዘ ሰው ባይኖርም ከሌሎች ሀገራት ጋር ባለን ቅርርብ ከስጋት
ነፃ አያደርገንም ያሉት ሚኒስትሩ ማህበረሰባችን ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር መሳይ በበኩላቸው በሀገራችን ባሉት ወቅታዊ የጤና ችግሮች ላይ የህብረተሰቡ መዘናጋት ምክንያት
የስርጭት ሁኔታው መጨመሩን ገልፀዋል፡፡ ለዚህ ችግር መፍትሄ ለመስጠት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ የጤና ባለሙያዎችም የማማከር ድጋፍ እንዲያደርጉ
እና ሚዲያዎችም ተገቢውን እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በአንዳንድ የዓለም ሀገራት የተከሰተው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ለመከላከል የቅኝትና ምላሽ ስራዎችን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በጋራ
እየተሰራ መሆኑን አውስተው በሽታውን ለመከላከል የዓለም የጤና ድርጅት ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት መከላከያ መንገዶችን መተግበር አስፈላጊ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡