በደቡብ ክልል የተሰጠው የመስክ ኢፒዲሞሎጂ ስልጠና ተጠናቀቀ
በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ ለሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ባለሙያዎች የተሰጠው መሰረታዊ የመስክ ኤፒዲሞሎጂ ስልጠና ከሶስት ዙር ስልጠና በኋላ የተጠናቀቀ ሲሆን በዚህ ስልጠና 24 ከደቡብ 3 ባለሙያዎች ደግሞ ከኦሮሚያ የተውጣጡ ሲሆን በስተመጨረሻም ላይ ሁሉም ሰልጣኞች በየምድብ ወረዳዎቻቸው የሰሩትን የጥናት ስራዎቻቸውን አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
አቶ ጃፈር ከዛሊ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል የዝግጁነትና የአቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ባለሙያ እና የስልጠናው አስተባባሪ እንደገለጹት ስልጠናው በሶስት ዙር የተሰጠ ሲሆን፤ ከመሰረታዊ የኮምፒውተር አውቀት፣ የበሽታ ቅኝት መረጃ እንዴት እንደሚሰባሰብ ማካታት ያለበትን እና ለሚመለከተው አካል እንዴት ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እንደሚቀርቡ እንዲሁም ወረርሽኝ ቢከሰት ምን መደረግ አለበት መንስዔውስ ምንድነው የሚለውን ጨምሮ በሶስቱ ዙር ስልጠናው ውስጥ የተካተቱ እንደነበር ጠቅለል አድርገው አስረድተዋል፡፡
በስተመጨረሻም ስልጣኞች የምስክር ወረቀታቸውን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ፣ ዶ/ር ታጠቅ ቦጋለ የአፍሪካ ፊልድ ኢፒዲሞሎጂ ኔትዎርክ (AFENET) ሪጅናል ቴክኒካዊ ዳይሬክተር እና አቶ ተስፋጺሆን ተረፈ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በተገኙበት የተቀበሉ ሲሆን ከዛም በፊት ከሰልጣኞች ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ሶስቱም ተገቢውን ምላሽ እና አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡