በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአዲስ መልክ የተደራጀዉ የሕብረተሰብ ጤ
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአዲስ መልክ የተደራጀዉ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ተመረቀ።
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአዲስ መልክ የተደራጀዉ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቆ በይፋ ስራ ጀመረ።
በመርሀ ግብሩ የተገኙት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት ይህ ማዕከል ከጤና ሚኒስቴርና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ለኮቪድ-19 እና ሌሎች ወረርሽኞችን ለመግታት ምላሽ መስጠትና የማስተባበር ስራዎችን እንደሚሰራ ተናግረዋል። አክለውም ይህንን ማዕከል በሁሉም ክልሎች እና በተመረጡ ዞኖች ላይ አቋቁሞ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል መረጃዎችን የማሰባሰብ፣ የመተንተን እና ለውሳኔ የሚረዱ ማስረጃዎችን የማዘጋጀት ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ በበኩላቸው
የዚህን የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ለማቋቋምና በአዲስ መልኩ ለማደራጀት በሰው ሀይል፣ በገንዘብ፣ በግብዓት፣ በተለያዩ ስራዎች ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አጋር ድርጅቶች በተለይም ለUS-CDC እና ICAP በእንስቲትዩቱና በራሳቸው ስም ከፍ ያለ ምስጋና በማቅረብ የከተማ አስተዳደሩን የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል በአዲስ መልክ በማደራጀት እና በማሻሻል በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየሰራ ያለውን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮን ከልብ በማመስገን ይህንን ስራ ቀጣይነት ለማረጋገጥና ለማጠናከር የከተማ አስተዳደሩ አመራርና በየደረጃው ያለው አካል ሃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ንግግራቸውን በመጀመር የጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ICAP እና CDC የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ እየሰራ ላለው የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን መከላከልና መቆጣጣር ስራ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይም ድጋፍቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል ።
የ ICAP ዳይሬክተር ዶ/ር ዘነበ መላኩ በበኩላቸው ICAP ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል እና ላቦራቶሪ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱንና በቀጣይም አሰፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
በዕለቱም የኢትዮ ፈረንሳይ የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማዕከል እና የድሬዳዋ ሪጅናል ላብራቶሪ ጉብኝት ተደርጓል።