በጌምቤላ ክልል በጎግ ወረዳ ጊኒዎርም ለማጥፋት እየተሰሩ ያሉ ሰራዎችን በተመለከተ የመሰክ ምልከታ ተደረገ
የኢፌዴሪ ጤና ሚኒሰተር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንሰትትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰቻለዉ አባይነህ እና የክልሉ ኘሬዝዳንት እንዲሁም ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና አጋር አካላት በተገኙበት በጌምቤላ ክልል በጎግ ወረዳ ጊኒዎርም ለማጥፋት እየተሰሩ ያሉ ሰራዎችን በተመለከተ የመሰክ ምልከታ አደረጉ።
የጤና ሚኒስተር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት በቅድሚያ ላለፋት ዓመታት የጊኒ ዎርም በሽታን ለማጥፍት እየተደረገ በነበረው ከፍተኛ ጥረት ከጎናችን ለነበሩት አጋር ድርጅቶች እንዲሁም የመንግስት አካላት ያላቸውን ከፍተኛ አድናቆት እና ምስጋና ገልጽዋል።
የዚህ የመስክ ጉብኝት አላማም በተለያዩ እርከኖች ያለውን የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና ድጋፍ ማጠናከር እና እውን ማድረግ እንዲሁም የበሽታ ስርጭት ባለባቸው ወረዳዎች እና በሰፈራ መንደሮች የንፁህ ውሃ አቅርቦት ችግርን እንደ አስፈላጊነቱ በአዲስ መልክ በመጠገን ወይም መልሶ በማቖቖም የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት ለማዳረስ ሴክተሮች ሁሉም ባለድርሻ አካላት እና አጋሮች ያለውን ቁርጠኝነት የበለጠ ማጠናከር የበሽታውን ስርጭት መግታት ብሎም በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ በሽታውን ለማጥፋት ተግተን መስራት እንዳለብን ገልፁዋል።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሃይሉ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም የጊኒዎርም በሽታ ትኩረት ከሚሹ የሕብረተሰብ ጤና ችግር ከሆኑ በሽታዎች መካከል አንዱ መሆኑን አስታውሰው ኢትዮጵያ ይህን በሽታ ከሀገራችን ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት እያደረገችና በዚህም ጥሩ ውጤት እየታየ ያለ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም በሽታውን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እንዲሁም ከሀገራችን ለማጥፋት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላትና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር እንደሚሰራና ለተደረገው ከፍተኛ አቀባበል በማመስገን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በመቀጠልም የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መ/የጤና ቢሮ ሃላፊ ክቡር አቶ ሮት ጋትዌች፣የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ቴንኩዌይ ጆክ ፣የግብርና ምኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ ፣ዶ/ር ደላሚኒ ኖሃ የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ምክትል ተጠሪ፣ አዳም ዌስ በአትላንታ የካርተር ሴንተር የጊኒ ዎርም መከላከያ የፕሮግራም ዳይሬክተር ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም ጊኒ ዎርምን ከኢትዮጵያ አጥፍቶ የሰርተፍኬት ተሸላሚ ለማድረግ ተባብረውና ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
በዕለቱም በጎግ ወረዳ ገረጋንቲ የዉሃ ኩሬ የሚታከምበት እና አታቴ ቀበሌ ገጠር ዉሃ አቅርቦት እና ለሕብረተሰቡ የመጠጥ ውሃ በሶላር የሚሰራ የጉድጓድ ዉሃ እና የጋ/ህ/ብ/ክ/ኛዋሃ/ዞን ፒኝውዶ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተጎብኝቷል።