ተቋማት ለማሕበረሰቡ በሚሰጧቸው የተለያዩ አገልግሎቶች ውስጥ የስርዓተ-ጾታና የአካል ጉዳተኞችን ጉዳይ ማካተት እጅግ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
May 24, 2023
የኢንስቲትዩቱ የሴቶች፣ህጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ለኢንስቲትዩቱ የማኔጅመንትና ቡድን አስተባባሪዎች ኢንስቲትዩቱ ለሕብረተሰቡ በሚሰጠው የተለያዩ የጤና አገልግሎቶች ስርዓተ -ጾታን እና የአካል ጉዳተኞችን ጉዳዮች በማካተት ተግባራዊ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ስልጠና በሁለት ዙር በቢሾፍቱ ከተማ ስልጠና ሰጠ፡፡
ወ/ሮ ማርታ አበራ የኢንስቲትዩቱ የሴቶች፣ህጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በስልጠና ፕሮግራሙ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንደገለጹት የስልጠናው ዓላማ የስርዓተ -ጾታና የአካል ጉዳተኞችን ጉዳይ ኢንስቲትዩቱ በሚሰጣቸው የተለያዩ የሕብረተሰብ ጤና አገልግሎቶች እና የዕለት ከዕለት የጤና አገልግሎቶች ውስጥ በማካተት ተግባራዊ እንዲደረጉ ለኢንስቲትዩቱ የባላይ ኃላፊዎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተሰጠ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አቶ ዘውዱ ጉሉማ ከጤና ሚኒስቴር አካታች የጤና አገልግሎት እና ሽግግራዊ መፍትሔ ለኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተደራሽነት በሚል ርዕስ በስፋትና በጥልቀት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡ ሲሆን ወ/ሮ ፋጡማ ሰዒድ ከጤና ሚኒስቴር አጠቃላይ ስለ ስርዓተ-ጾታ ማካተት የተዘጋጀ ማንዋልን መሰረት በማድረግ ሰፊ ማብራሪያ እና ገለጻ አድርገዋል፡፡