ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለሕብረተሰብ ጤና መሻሻል የሚኖረው ፈይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለጠ
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አንጻር እና የቤት ዉስጥ አየር ብክለትን በማስወገድ አንዲሁም ተያያዥ ህመምን እና ሞትን በመከላከል ረገድ ከፍተƒ አስተዋኦ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር ያጠናዉ ጥናት አመላከተ፡፡
ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስትር የጥናቱ ውጤት ይፋ በሆነበት መድረክ ላይ እንደገለጹት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፋይዳን አስመልክቶ የተሰራው ጥናት እጅግ አመርቂና አዳዲስ ያልተፈተሹ እይታዋችን ያመላከተ በመሆኑ መሰል ጥናቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡ ለእዚህም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሚደረጉት ምርምርና ጥናቶች የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡ ዶ/ር ሊያ አክለውም የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በጤናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ ተጽዕኖ ስለሚኖረው በጤናው ዘርፍ ዘላቂ የልማት ግብን (SDG) ለማሳካትም ትልቅ እገዛን እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ኤባ አባተ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሀገሪተን የኤሌትሪክ አቅርቦት አቅም ስለሚያሳድገው የጤናው ሴክተርም በየኤሌትሪክ አቅርቦት መቆራረጥና መጥፋት የተነሳ በጤናው ዘርፍ የዕለት ተዕለት ስራ ላይ ያጋጥም የነበረውን Áና እንደሚያስወግድ አብራርተዋል፡፡ ዳይሬክተር ጀነራሉ በበኩላቸው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከሀገራችንም አልፎ ለአባይ ተፋሰስ ሀገራት የሚሰጠው ጠቀሜታ የጎላ እንደሆነ ገልጸው ሌሎች መሰል ጥናቶች ወደፊት ሲከናወኑ የአባይ ተፋሰስ ሀገራትን አካቶ ቢጠና ለቀጣይ ውሳኔዎችና ትግበራዎች የሚኖረው ፋይዳ ከፍተƒ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
አቶ አማኑኤል ሉሉ የህዳሴው ግድብ ከጤና ምጣኔ አንጻር እንዲሁም ዶ/ር አወቀ ምስጋናው የህዳሴው ግድብ ከህብረተሰብ ጤና አንጻር በሚል ርእስ ያዘጋጁትን ጥናታዊ ጽሁፎቻቸውን አቅርበው ውይይቶች ተካሂዶባቸዋል፡፡
በምስራቅ አፍሪካ ባሉ የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ከኤሌትሪክ ሀይል እጦት ምክንያት በሚጠቀሙት የማገዶ Ãስ የተነሳ በቤት ውስጥ በሚፈጠር የአየር ብክለት የተነሳ በየአመቱ እሩብ ሚሊየን ሰዎች ይሞታሉ፡፡ ባለፉት 30 አመታት ሶስት ሚሊየን ወገኖቻችንን ለሀይል አገልግሎት በሚጠቀሙት የማገዶ Ãስ በቤት ውስጥ በሚፈጠር የአየር ብክለት የተነሳ እንደዋዛ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በመሆኑም ጥናቶች እንደሚያሳዩት የህዳሴው ግድብ ወደ አገልግሎት ሲገባ የወገኖቻችን ህይወት ከመቀጠፍ ይድናል፡፡ በአማካይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በመጀመሪያዎቹ ስምንት ዓመታት በ2.3% ሊያድግ ይችላል፡፡ ይህም የመንግስት እና የቤተሰብ ፍጆታን በ2.5% ይጨምራል ፡፡ የሀገር ኢኮኖሚ 4.5 በመቶ የመንግስት ፍጆታ 4.2 በመቶ እና የቤተሰብ ፍጆታ 4.4 በመቶ ይጨምራል፡፡ እነዚህ የሚያሳዩት በኋለኞቹ ዓመታት ከግድቡ የሚገኘው ጥቅም ከአመት ወደ አመት እየጨመረ እንደሚሄድ ሲሆን ሀገሪቱም ከፍተኛውን መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ጥቅሎችን ሽፋን ልታሳካ እንደምትችል ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያም ሆነች የተፋሰሱ ሀገራት ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ችግር ከሚታይባቸው መካከል ሲሆኑ ከሁለት አመት በፊት በተሰራ አንድ አለም አቀፍ ጥናት መሰረት የግብፅ የኤሌትሪክ ሽፋን 100% (መቶ በመቶ ሲሆን) ፤ ኬንያ 75% ፤ ሱዳን 60% ፤ ኤርትራ 50% ፤ ኢትዮያ 45%፤ ኡጋንዳ 43%፤ ታንዛንያ 36% ፤ ሩዋንዳ 35%፡ ደቡብ ሱዳን 28%፡ ዲሞክራቲክ ኮንጎ 19%፡ ቡሩንዲ 11 በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽፋን አላቸው፡፡
በቤት ውስጥ አየር ብክለት አጋላጭነት ከሚመጡ ዋና ዋና በሽታዎች መካከል በሆነው የሳንባ ምች (ኒሞንያ) የተነሳ እንደ ዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ለቤት ውስጥ አየር ብክለት የተጋለጡ ህፃናት (ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ) በኒሞኒያ የመያዝ ዕድላቸው በእጥፍ ይጨምራል፡፡ በመሆኑም በኒሞኒያ ከሚሞቱት ህፃናት ለ45% የሚሆኑት ህፃናት የመሞት ምክንያት ነው፡፡ይህም በበኩሉ የሀገሪታን የኢኮኖሚ አቅም አብሮ ስለሚጡያሳድገውመሰረት በጤናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ ተጽዕኖ አንደሚኖረዉ አሳይቷል፡፡